በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ በጄነቫ

የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ።

የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ ።

ኮሚሽነሩ ይህን ያሰጠነቀቁት ጄነቫ ውስጥ በተጀመረው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ መክፈቻ ላይ ነው።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ወዲህ የዓለምን ስርዓት ለማረጋጋት የተደረጉ በርካታ ክንዋኔዎች በአሁኑ ወቅት እያደገ በመጣው የተራውን ሕዝብ ብሶትና ሥጋት የፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረግ ተግባር የመፈራረስ አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሺነር ዜይድ ራአድ አል ሁሴን አስጠንቅቀዋል።

ከአውዳሚው የዓለም ጦርነት በተከተሉት ሰባ ዓመታት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች ዘላቂ ሠላምና ልማት ዕውን ሊሆን የቻለው በመንግሥታቱ ድርጅት ቻርተርና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውሎች የተደነገጉት መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች በመከበራቸው ነው ብለዋል።

የፖለቲካ መሪዎች በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ላይ ለሚያካሂዱዋቸው የክፋት ዘመቻዎች ወይም ደግሞ ለእነዚህ መብቶች ከቆሙ ውሎች እንወጣለን ብለው ለሚያሰሙት ዛቻ ከተንበረከክን ዓለማችን ከባድ ጉዳት ያገኛታል ሲሉ ከፍተኛው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር አስጠንቅቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሣምንታዊ የስፖርት ዝግጅት

  • ሰሎሞን ክፍሌ
ጃፓን ቶክዮ ማራቶን

በ1ሺኽ 5 መቶ የዓለም ሻምፒዮኗ ገንዘቤ ዲባባ በዓለም አቀፉ የ ቪልላ ድ ማድሪድ አንድ ሺኽ ሜትር ሩጫ ውድድር የግልዋን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ አሸነፈች።

በ1ሺኽ 5 መቶ የዓለም ሻምፒዮኗ ገንዘቤ ዲባባ በዓለም አቀፉ የ ቪልላ ድ ማድሪድ አንድ ሺኽ ሜትር ሩጫ ውድድር የግልዋን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ አሸነፈች።

በቶክዮ ማራቶን ደግሞ የኬንያ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጁ።

በእግር ኳስ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ፕሪምየር ሊግ ዜናዎች ተጠናቅሯል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Ethiopia's State of Emergency

የኦሮምያና የሶማሌ ክልል አዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች በታጣቂዎች ለሚፈፀምው ጥቃት መፍትሄ ለማስገኘት በአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስትና በሁለቱ ክልሎች ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

ከኦሮምያ አዋሳኝ ቦታዎች የሚወጡ ያሉዋቸው ታጣቂዎች በክልላቸው አዋሳኝ ወረዳዎች ጥቃት እየተፈፀመ መሆናቸውን የተናገሩት የሶማሌ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽንስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማዔል ናቸው፡፡ ታጣቂዎቹ የኦሮምያን መንግሥት ሕዝብንና ተቋማቱን የማይወክሉና በውጭ ያሉ ፀረ ሠላም ኃይሎች የሚመሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ጥቃት የሚፈፅሙ ኃይሎችን በተመለከተ የሁለቱ ክልላዊ መንግሥታት ግምገማ ተመሳሳይ አለመሆኑ ይታያል፡፡ ጥቃት እየፈፀሙ ያሉት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚነሱ ነገር ግን ሕዝቡንም ሆነ ክልላዊ ተቋማቱን የማይወክሉ ታጣቂዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በቀለ ገርባ

በቀድሞ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በአቶ በቀለ ገረባ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የሲዲ ወይንም የድምፅ ከምስል ማስረጃ ዛሬም በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሊታይም፣ ሊደመጥም እንዳልቻለ ተገለፀ፡፡

በቀድሞ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በአቶ በቀለ ገረባ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የሲዲ ወይንም የድምፅ ከምስል ማስረጃ ዛሬም በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሊታይም፣ ሊደመጥም እንዳልቻለ ተገለፀ፡፡

ተከሳሽና የተከሳሽ ጠበቃ ይሕ የዓቃቤ ሕግ ማሰረጃ እንዲታለፍ ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ የአጭር ጊዜ ቀጥሮ ሰጥቶ ዓቃቤ ሕግ ማስረጃውን እንዲያቀርብ አዘዘ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

መኢአድ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ሰብሳቢ ከየካቲት 7 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታወቀ፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ሰብሳቢ ከየካቲት 7 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታወቀ፡፡ አባሎቻችን እየታሠሩ ያሉበት ሁኔታ ሊካሄድ በታቀደው ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሣድር ይችላል ብለዋል - የፓርቲው ዋና ፀኃፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዛሬ እንዳስታወቀው የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ዞን ሰብሳቢ የሆኑት ሻምበል ንጉሴ ደርሶ ለአለፉት ሁለት ሣምንታት በእስር ላይ ናቸው፡፡

የፓርቲው ዋና ፀኃፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት ከፍተኛ አመራሩ የታሠሩት ጭልጋ ወረዳ ወደ ምትገኝ "ጉባዔ" በተባለች ቀበሌ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ እንደሄዱ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG