በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ረቡዕ 1 የካቲት 2017

በነሐሴ ወር የቃጠሎ አደጋ የደረሰበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል እና ለ23 ሰዎች ሞት ተጠያቂ ናችሁ በሚል የተከሰሱ 38 እስረኛ ተከሳሾች ጨለማ ቤት መታሰራቸውንና ከቤተሰብ መገናኘት እንዳልቻሉ በመግለፅ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እነ ማስረሻ ሰጤ ብሬ በሚል የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ በ23 ታራሚዎች ግድያና በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው የ38 እስረኛ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ ላቀረበው አቤቱና የተከሳቹ ጠበቆች መቃወሚያ አቀረቡ።

እስረኞቹ ጭለማ ቤት እንደታሰሩና በቤተሰብ መጎብኘት እንዳልቻሉ ለችሎቱ መናገራቸውን በዛሬው ዕለት በችሎት ላይ የተገኙ የአምስት ተከሳሾች ጠበቃ አቶ ሰኢድ አብደላ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አማንዳ ቤኔት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር

"የአሜሪካ ድምጽ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ የተቋቋመብትን ዓላማ ለማሳካት በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች መረጃ ማሰራጨቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለጽ እወዳለሁ። እውነተኛ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛና የማይወግን የዜናና መረጃ ላለፉት 75ዓመታት እንዳሰራጨን ሁሉ ለቀጣይ 75 ዓመታት የምናደርገውም ይሄንኑ ነው።"አማንዳ ቤኔት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ስርጭት የጀመረበትን 75ኛ ዓመት፣ ዛሬ እአአ የካቲት 1 ቀን እያከበረ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር አማንዳ ቤኔትን የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው ነበር፡፡

"የአሜሪካ ድምጽ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ የተቋቋመብትን ዓላማ ለማሳካት በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች መረጃ ማሰራጨቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለጽ እወዳለሁ። እውነተኛ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛና የማይወግን የዜናና መረጃ ላለፉት 75ዓመታት እንዳሰራጨን ሁሉ ለቀጣይ 75 ዓመታት የምናደርገውም ይሄንኑ ነው። በግሌ እዚህ የአሜሪካ ድምጽ አካል ሆኜ፣ ከእናንተና ከሌላው ዓለም ጋር ስነጋገር፤ በቅድሚያ ለምን ጋዜጠኛ ለመሆን እንደወሰንኩ ያስታውሰኛል። የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት እኔም፤ እዚህ አብረውን የሚሰሩ ባልደረቦቼም ዝግጁ ናቸው። 75ኛ ዓመታችንን ስናከብር፤ ለቀጣይ 75 ዓመታት እንድትከታተሉን እየጋበዝኩ ነው።"አማንዳ ቤኔት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይልና ቪድዮ ይመልከቱ።

አሜሪካ ወደ ሃገርዋ የሚመጡ የውጭ ሃገር ሰዎች ላይ ገደብ ስታደርግ የመጀመሪያ ጊዜያዋ አይደለም፡፡ ታዲያ በዜግነታቸው እየለየች “አትምጡብኝ፡” ብላ ታውቃለች እንዴ? “እንዴታ!”

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የፈረሙዋቸው የኢሚግሬሽን ማስፈፀሚያ ትዕዛዞች በቅርብ ዘመናት የአሜሪካ ታሪክ እንዲህ ያለ መመሪያ ሲወጣ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል። ዩናይትድ ስቴትስ በምትቀበላቸው የውጭ ሃገር ሰዎች ላይ ገደብ ስታደርግ ግን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።

እኤአ በ1789 ዓ.ም የተደነገገው የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግሥት የኢሚግሬሽን ሕግን ሙሉ ሥልጣን ለሀገሪቱ ለምክር ቤቱ ሰጡዋል።

ፕሬዚደንቱ ደግሞ ሕጎቹን በመመሪያዎች አማካይነት እየተቆጣጠረ ያስፈፅማል ይላሉ

“ዘ ወርድስ ዊ ሊቭ ባይ” በሚል ርዕስ ስለ ሕገ መንግሥቱ የሚያወሳ መፅሃፍ የደረሱት ሊንዳ ሞንክ።

በመጀመሪያዎቹ የአንድ መቶ ዓመታት የአሜሪካ ታሪክ ታዲያ ኮንግሬሱ በኢሚግሬሽን ሕጉ ላይ በፌዴራሉ መንግሥት ደረጃ ገደብ የሚጥል ደምብ አውጥቶ አያውቅም። ብዛት ያላቸው የአየርላንድ እና የጀርመን ተወላጆች ወደዩናትድ ስቴትስ ፈልሰው የሰፈሩትም በእነዚህ ዓመታት ነው።

ብዙዎች የቻይና ተወላጆችም በ1860ዎቹ ዓመታት በባቡር መሥመር ዝርጋታ ሥራ በወዛደርነት ሊሰሩ መጥተው እዚሁ ቀሩ።

ታዲያ አገሬው አሜሪካኖች መጤ በብዛት መስፈሩን አልወደዱትም ነበር። አንድም የብዙዎቹን ከአይርላንድ እና ከጀርመን የፈለሱት መጤዎች ተከታዮች የካቶሊክ ክርስትና እምነት ባለ መውደድ ሲሆን እስያውያኑን ደግሞ ወንጀለኞች ሴትኛ አዳሪዎች ወይም ደግሞ ሥራችንን ይሻማሉ ብለው ይጠሉዋቸው ነበር።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG