በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የ2017 የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የደህንነት ኮሚሽነር በሊቢያ ያለው ሁኔታ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን አመልከተ፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የደህንነት ኮሚሽነር በሊቢያ ያለው ሁኔታ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን አመልከተ፡፡

የተቋቋመው መንግሥትም ለሕዝቡ ኑሮ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንኳን መስጠት እንደተሳነው አስታውቋል፡፡ በአሁጉሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የሰላም እና የደህንነት ችግሮችን አመላክተው ዓለም አቀፍ ትብብሩ እንዲጠናከር አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባዔ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር እስማኤል ቸሩ ጉኡይ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደህንነት ኮሚሺን ኮሚሺነር ዛሬ በሕብረቱ ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሁን ያለው የሊቢያ ሁኔታ ለሁላችንም በእጅጉ አሳሳቢ ነው ሲሉ በአፅዕኖት ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የደህንነት ኮሚሽነር በሊቢያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:26 0:00

በዘንድሮ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ54ቱ አባል ሀገሮች 39ኙ ሞሮኮ ተመለሳ ሕብረቱን እንድትቀላቀል ድጋፍ በመስጠታቸው አሸናፊው "አንድነት" ሆኗል።

ሞሮኮ ከአህጉራዊው ድርጅት ለሰላሳ ዓመታት በላይ ተለይታ ከቆየች በኋላ እንደገና መመለሷን የአፍሪካ ኅብረት በደስታ ተቀብሎታል። ሀገሪቱ እ.አ.አ በ 1984 ዓ.ም ከኅብረቱ እንድትወጣ ያደረጋት ዓብይ ምክንያት መፍትሄ ካላገኘ ግን ሽግግሩ የተሳካ ላይሆን ይችላል። አኒታ ፓወል ከአዲስ አበባ ያደረሰችን ዘገበ አለ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG