በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፋሲል ግንብ

የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ተጨማሪ የሽብር ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ሊካሄድባቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጉዳይ የሚታየው ጎንደር ላይ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ተጨማሪ የሽብር ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ሊካሄድባቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡

ኮ/ል ደመቀ አሁንም ክሥ ያልተመሠረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው ከትናንት በስተያ፤ መስከረም 18/2009 ዓ.ም የታየው በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ መክት ካሣሁን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በግድያ ወንጀል የጠረጠራቸው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በዕለቱ ተዘግቶ አቃቤ ሕግ ክሥ ይመሠርት ወይም ሌላ ሃሣብ ያቀርብ እንደሆነ የ15 ቀናት ጊዜ ያለው መሆኑን አቶ መክት ገልፀው አዲስ ለተከፈተው ምርመራ ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን ቀጠሮ ጠይቆ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

እርሣቸውና ደንበኛቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 2/2009 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ የአካባቢው ሕዝብ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ እንዲታይ መወሰኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የእሬቻ በዓል የማንም ጣልቃ ገብነት አያስፈልገውም - ኦፌኮ

እሬቻ

የእሬቻ በዓል የሕዝብ መሆኑን ያስታወቀው የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ የማንም ጣልቃ ገብነት አያስፈልገውም ብሏል።

በእሬቻ በዓል ስም የፖለቲካም ሆነ የግል ፍላጎታቸውን በሕዝብ ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው ሲል የገዢው ፓርቲና የክልሉ መንግሥትን ወንጅሏል።

በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ታዳሚዎች በዓሉን ከዳንኪራ ይልቅ በመዝሙር እኛ በዝምታ እንዲያከብሩ ጥር አቅርቧል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የእሬቻ በዓል የማንም ጣልዋ ገብነት አያስፈልገውም - ኦፌኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:03 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG