በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አቶ ሃብታሙ አያሌው በሆስፒታል ከቤተሰቦቹ ጋር

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሀገር ወጥቶ እንዲታከም የቀረበውን የእግድ ይነሳልን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አቶ ሀብታሙ በሀገር ውስጥ መታከም እንደማይችልና ሕክምናውን ከሀገር ውጪ ማድረግ አለበት የሚል በዶክተሮች የተወሰነ ማስረጃ ካቀረባችሁ በማንኛውም ሰዓት እግዱ ይነሳል እንደተባሉ ጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ ሀብታሙ አያሌው ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መምሪያ በነበረበት ወቅት፤ የጀመረው ሕመም ተባብሶ ራሱን መርዳት በማይችልበት ሁኔታ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ በትናንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ መግለጻቸው ይታወሳል።

በሀገር ውስጥ የሚገኘው ሕክምናም ለሌላ ስቃይ የሚዳርገውና ሕይወቱን ለአደጋ የሚጥለው እንደሆነ በመግለፅ ከአገር ወጥቶ መታከም እንዲችል ቢጠይቅም ፍርድ ቤት በጣለበት እግድ ምክንያት ከሀገር መውጣት እንዳልቻለና ይህ እግድ እንዲነሳለት በጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገብተው ዛሬ ይታያል መባላቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

በዛሬው ዕለት የእግድ ይነሳልን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አቶ ሀብታሙ በሀገር ውስጥ መታከም እንደማይችልና ሕክምናውን ከሀገር ውጪ ማድረግ አለበት የሚል በዶክተሮች የተወሰነ ማስረጃ ካቀረባችሁ በማንኛውም ሰዓት እግዱ ይነሳል እንደተባሉ ጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአቶ ሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ውሳኔ አላገኘም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ቤት መፍረሱን የተቃወሙ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ መስተዳድር ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ አቤቱታ ሲያቀርቡ

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለመዶ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ቀርሳ፣ ኮንቱማ እና ማንጎ ጨፌ በተባሉ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤታቸው በዶዘር እየፈረሰና ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለመዶ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ቀርሳ፣ ኮንቱማ እና ማንጎ ጨፌ በተባሉ አካባቢዎች ዕረቡ ዕለት ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። የአካባቢው ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤቶቹ ከትናንት ጀምሮ በዶዘር እየፈረሰባቸው እደሆነና ወንዶች ወደ አካባቢው እንዳይገቡ እንደተከለከሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ማምሻውን ነዋሪዎቹን አነጋግሯል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

“የአምስት ቀን አራስ ልጄን እንደያዝኩ ጥዬ ሸሽቻልሁ” አንዲት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG