በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የጋና ምርጫ ኮሚሽን ትናንት የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊና የምክር ቤት አባላት ምርጫ የድምፅ ውጤት ቀስ በቀስ ይፋ እያደረገ ነው፡፡

ኮሚሽኒ በአንድ አንድ አካባቢዎች ከተመዘገበው መራጭ በላይ የሆነ ድምፅ ተሰጧል፤ ሌሎችም ጣልቃ ገብ ተግባራት ተፈፅመዋል የሚሉ አሉባልታዎች እየተናፈሱ ስለሆነ ቆጠራውን በከፍተኛ ጥንቃቄ ለማከናውን ብለን ነው ሲል አስታውቋል፡፡

ገዥው ፓርቲ እና ተቃዋሚዎች ግን ውጤቱን በየፊናቸው እየተናገሩ ነው፡፡

የጋና ምርጫ ኮሚሽን የፕሬዚዳንታዊና የምክር ቤት አባላት ምርጫ የድምፅ ውጤት እያስታወቀ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00

የኦክላሆማ ጠቅላይ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስካት ፕሩዪት

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካቢኔአቸውን እያዋቀሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አሜሪካዊያንም ዓለምም እነማንን እያነሱ ለየጉዳዩ አውራ እንደሚያደርጉ በንቃት እየተከታተሉ ነው፡፡

የአሜሪካዊያን የውስጥ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዓለምም ሥጋትና ትኩረት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የዓለማችን የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና የዓለማችን ግለት በእውኑ እጅግ አንገብጋቢ ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

​የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሰጧቸው ካሉ የሰሞኑ ሹመቶች መካከል ለሃገራቸው የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ድርጅት አለቃነት የሰየሟቸው የኦክላሆማ ጠቅላይ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስካት ፕሩዪት “የአየር ንብረት ለውጥ የለም” ብለው ከሚያምኑ አሜሪካዊያን አንዱና እንዲያውም ተሟጋችም ናቸው፡፡

ይህ የሚስተር ትራምፕ ሹመት ዛሬ ብዙዎችን እያነጋገረና እየፈተነ ያለ ውሣኔ ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ለአካባቢ ጥበቃ ትራምፕ ሰው ሾሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG