በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሴናተር ክሪስ ኩንስ

“ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አስተዳደር እያመራ ያለበትን አዝማሚያ የሚጠቁም ሌላ አዋኪ ምልክት ነው። ውስብስቡን ውስጣዊ የፖለቲካና የክልል አወቃቀር፤ እንዲሁም ከባድ ሊሰኙ የሚችሉትን ታሪካዊ ገጠመኞቻቸውን እገነዘባለሁ። ይሁንና መንግሥቱ በቅርቡ የወሰዳቸው የኃይል እርምጃዎች ግን ዘለቄታ ላለው ዲሞክራሲ ተጨባጭ አደጋዎች ናቸው።” ሴናተር ክሪስ ኩንስ በየዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አባል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ ያሳሰባቸው መሆኑን አንድ ሌላ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ተናገሩ።

በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አባል ሴናተር ክሪስ ኩንስ በተለይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኢትዮጵያ መንግሥት ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አዝማሚያ እያመራ መሆኑን የሚጠቁም ነው፤ ሲሉም ያደረባቸውን ሥጋት ገልጠዋል።

የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉ መሆናቸውን የተናገሩት ሚር ኩንስ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በንግግር ነፃነት ላይ የጣላቸው ገደቦችም ሌላው አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው፤ ሲሉ ተችተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት “የኃይል እርምጃ” እና የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ትችት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00

የአረና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አምዶም ገ/ሥላሴ

የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ በዛሬ ዕለት ስለተካሄደው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የካቢኔ ሹመት አስተያየት ሰጥተዋል።

በዛሬው ዕለት የተካሄደውን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የስድስት ካቢኔ ሹመት አስመልክቶ የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየት ሰጥቷል።

“የሰዎች መቀያየር ለትግራይ ሕዝብ ችግሮች የሚሰጠው መፍትሔ አይኖርም” ብሏል።

ጽዮን ግርማ ማምሻው አነጋግራዋለች።

"የሰዎች መቀያየር ለትግራይ ሕዝብ ችግሮች የሚሰጠው መፍትሔ አይኖርም” አረና
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:16 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG