በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ፣ በሃያ ሦስት ታራሚዎች ግድያና በሽብር ወንጀል አቃቤ ሕግ ክሥ የመሠረተባቸው ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ “ግፍ ፈፅሞብናል” ሲሉ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት አሰምተዋል፡፡

ቀደም ሲል ለፖሊስ የሰጠነው ቃል ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈፅሞብን የሰጠነው ሰለሆነ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያድርግልን ሲሉም ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

አሥራ ሦስተኛ ተከሳሽ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ዛሬም አልቀረቡም፤ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ስለ እርሳቸው በቂ መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል፡፡

ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ “ግፍ ፈፅሞብናል” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

በአትሌቲክሱ የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን በበርካታ ዓለምቀፍ መድረኮች በበላይነት ያስጠራው ዝነኛው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በ72 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አትሌት ምሩፅ ይፍጠር የአርባ ዓመት ጎልማሳ በነበረበት ወቅት ነው ሁለት የወርቅ መዳሊያዎችን በ1980 የሞስኮ ኦሎፒክ ላይ ያስገኘው፡፡ በ1972 ሙዩኒክ ኦሎፒክም የነሃስ መዳሊያ ተሸልሟል፡፡

በቅፅል ሰሙ “ማርሽ ቀያያሪው ሯጭ” በመባል ይጠራ የነበረው ምሩፅ ይፍጠር በስደት ይኖርበት ከነበረው ካናዳ ለብዙ ጊዜ ታሞ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

“ለእኔ እና ለኢትዮጵያ አትሌቶች ምሩፅ ዋነኛ አነቃቂያችን ነው” ያለው ታዋቂው ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ “ለእኔ ከዚህ መድረስ ምክንያት ነው” ሲልም አወድሶታል፡፡ ወንድ ልጁ ቢንያም ምሩፅ በበኩሉ ሲናገር አባቱ ለረጅም ጊዜ የመተንፈስ ችግር እንደነበረበት አስረድቷል፡፡

ምሩፅ ይፍጠር የሰባት ልጆች አባት ነበር፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG