በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በመገባደድ ላይ የሚገኘው የአውሮፓዊያን ዓመት 2016 ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ሁለት ከበባድ ፈተናዎች ደቅኖ ያለፈ ሆኗል። የኢትዮጵያ መንግሥትና የዓለምቀፍ ድርጅቶችም እንዳስታወቁት ከ1977ቱ የከፋና ከ10ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠ ድርቅ ተከስቷል።

በተጨማሪም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ሀገሪቱ በከባድ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ስትታመስ ቆይታ፤ በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተዳደር ላይ ትገኛለች። በዛሬው የንግድና ምጣኔ ሀብት ዝግጅት የዓመቱን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎችና ተፅዕኖዎችን እንገመግማለን።

ቀዳሚው ከአዲስ አበባ ዶር ደምስ ጫን ያለው ናቸው። በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲዎች በተለይ በግብርናና አርብቶ አደር ምጣኔ ዙሪያ መጽሃፍ ያሳተሙ ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያ ምጣኔ ተፅዕኖዎቹን ተቋቁሞ ለማደግ ችሏል ይላሉ።

የአለም የገንዘብ ድርጅት/IMF/ የኢትዮጵያ ስራ መሪ ሁሊዮ ስኮላኖ በኢትዮጵያ እድገት ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀን፤ በሚያዝያ ወር ከወጣው የ4.5 ከመቶ የምጣኔ ሀብት እድገት እንዴት ወደ 6.5 ከመቶ ከፍ ያለ ተመን ላይ እንደደረሱ ሲያስረዱ “በሰኔ ወር ባወጣንው ትንበያ ምጣኔው በ4.5 ከመቶ አንተ እንዳልከው እንደሚያድግ ገልፀን ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በክረምቱ መገባደጃ የእህል ምርትን በተመለከተ አዲስ አሃዝ አግኝተናል። እንደሚታወቀው የሰብል ምርቱ በድርቁ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። በዚህ የተነሳ የሰብል ምርት እንደሚቀንስ ገምተን ነበር። ሆኖም በነሐሴ ወር በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ይፋ የሆነው የግብርና ምርት አሃዝ ምርቱ በአጠቃላይ በ3ከመቶ መጨመሩን አስታውቋል።”

/IMF/ ለዓመቱ ማለትም ለ2015/16 በጀት አመት አስቀድሞ አውጥቶት የነበረውን 4.5 ከመቶ እድገት ትንበያ ወደ 6.5 ከፍ እንዲል አድርጓል።

ዶር አክሎግ ቢራራ ከ30 ዓመታት በላይ በአለም ባንክና ሌሎች ድርጅቶች ይሰሩ የልማት ምጣኔ ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በድርቁ የተነሳ ምርት የቀነሰበትና፤ ዓመቱን ሙሉ በተለያዩ የህገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሱ የጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን ያስተጓጎሉበት ስለሆነ፤ መጠነ ሰፊ አሉታዊ ተጽእኖዎች ይኖረዋል ይላሉ።

ዝርዝሩን ከውይይቱ ያዳምጡ

የኢትዮጵያ ምጣኔ ባለፈው አንድ አመት፡- ድርቅና የፀረ መንግሥት ተቃውሞዎችና ተፅዕኖዎቻቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:55 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ

ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት እንደሆነ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ አሳሰቡ፡፡

ለተዛባ ዜና እና ለጥላቻ ንግግር መድሃኒቱ በርን መዝጋት ሳይሆን በሃገር ውስጥ ነፃ፣ ተቀባይነትን ላገኘና ሕያው ለሆነ መገናኛ ብዙሃን በርን በሠፊው መክፈት እንደሆነም ጠቆሙ፡፡

በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ ሥርዓቱን ለዝነተ ዓለም ለማፅናት በሚደረግ ትግል ወይንም ሥርዓቱን በሃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን እንደማይችል አመለከቱ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ይህን የገለፁት ለቪኦኤ ብቻ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ከፖለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችና ከሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ስላከናዎኗቸው ተግባራትና በተለያዩ ርዕሶች ላይ መለስካቸው አምሃ አነጋግሯቸዋል፣ የመጨረሻውንና ክፍል ሁለትን እንሆ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የማሊኖውስኪ ኢንተርቪው ከቪኦኤ ጋር - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:41 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG