በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በጎተበርግ ስዊድን ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሠልፍ

በጎተበርግ ስዊድን ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬ የተቃውሞ ሠልፍ አካሂደዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈፀማል ያሉትን የመብት ረገጣ እና የግፍ ግድያ በማስመልከት፣ ለስዊድን መንግሥት፣ ይልቁንም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተቋማትና ድርጅቶች አቋማቸውን እንዲመረምሩ ለማሳሰብ ነው ሠልፍ የወጣነው ብለዋል፤ በጎተበርግ ስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፡፡

የሠላማዊ ሠልፉ አስተባባሪ የሆኑት የጎተቦርግ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ ለቪኦኤ እንደገለፁት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሠላም እጦት፣ በህዝቦች መካከል ያለውን የመካፋፈል ፖሊሲ፣ መንግሥት የሚያራምደውን እና የሠዎችን ሕይወት ማጥፋት ድርጊት ለመቃወም ነው የተሠባሰብነው ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሠልፍ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ተጠርጣሪዎቹ "በምርመራ ወቅት ከባድ የማሰቃየት ድርጊት ተፋጽሞብናል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል፤ ፍርድ ቤቱም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞውን የአንድነትና የሠማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትን ጨምሮ ሦስት መልስ ሰጪዎችን በነፃ ሲያሰናብት ሁለቱን ደግሞ የተከሰሱበትን፣ አንቀፅ ለውጦ እንዲከላከሉ ወስኗል።

ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤት ቅሊንጦ እስር ቤትን በማቃጠልና ሃያ ሶስት እስረኞችን ሕይወት በማጥፋት እንዲሁም በሚሊዮኖች ብር የሚገመት ንብረት በማውደም ፌዴራል አጠቃላይ አቃቢ ሕግ በሰላሳ ስምንት አስረኞች ክስ ምስርቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አቃቤ ሕግ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎና በሃያ ሦስት እሥረኞች ግድያ፣ በሰላሳ ስምንት ታራሚዎች ላይ የሽብር ክስ መሥርቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:20 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG