በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዶ/ መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር በታሰሩ በአሥራ አምስተኛ ቀናቸው ዛሬ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለብቻቸው በአንድ ክፍል የታሠሩ ቢሆንም በጤንነታቸው በኩል ደህና መሆናቸውን ጠበቃቸው ገልፀዋል።

ዶ/ር መረራ በሚቀጥሉት አሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ከሕግ ጠበቆቻቸው ጋር ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ “ሪፖርቱ የመንግስትን ምላሽ ያላካተተ የአንድ ወገን ሪፖርት ነው” ብሎታል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ነፃነትን በማፈን ሰብዓዊ መብትን ገድቧል” ሲል በዛሬው ዕለት ዝርዝር ሪፖርት አውጥቷል።

"የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ በተቀነባበረና ሕገወጥ በሆነ መንገድ ማኅበራዊ ሚዲያን፣ የዜና ማሰራጫና ድረ ገፆችን በመዝጋት የመንግስት ወታደሮች ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ላይ የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይታዩ አድጓል። በዚህ ድርጊትም ዜጎች ኢንተርኔት የማግኘት መብታቸው ተጠሷል። በተጨማሪም በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈፀሙ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለዓለም እንዳይታዩ አፍኗል" ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ “ሪፖርቱ የመንግሥትን ምላሽ ያላካተተ የአንድ ወገን ሪፖርት ነው” ብሎታል።

ጽዮን ግርማ ያዘጋጀችውን ዝርዝር ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን መብት ከማቀብና ኢንተርኔትን ከመገደብ እንዲቆጠብ አምነስቲ አሳስቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:30 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG