በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ጋምቤላ

የጋምቤላ እርሻ ባለሐብቶች የሕብረት ሥራ ማኅበር በማንነታችን ላይ ጫና በመፍጠር እና ከልማት ባንክ ይሠጠን የነበረው ብድር በመቆሙ ምክንያት ትልቅ ችግር ደርሶብናል ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበሩ መንግሥት አቤቱታችንን አዳምጦ ቀርቦም እንድንወያይ ችግራችንን በወቅቱ እንዲፈታልን እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የጋምቤላ እርሻ ባለሐብቶች ልማት ባንክን አማረሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት በነበራቸው ቀጠሮ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው ለችሎት ማስረዳታቸውን ጠበቃቸውና ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነ ከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነበራቸው ቀጠሮ ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ውስጥ በአምስት ተከሳሾች ላይ ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው አንድ ተከሳሽ አቤቱታ አቀረበ።

ጽዮን ግርማ በዛሬ ችሎት ተከሳሾቹን ወክልው ችሎት የቆሙትን ጠበቃ አቶ ሰኢድ አብደላና የአንዱን ተከሳሽ እናት አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

"በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞብናል" ተከሳሾች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG