በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ከነገ ውዲያ ማክሰኞ ይካሄዳል፤ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተንና ሪፐብሊካኑ ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ማንን እንደሚመርጡ እስካሁን ያልወሰኑ መራጮችን “እኔ እሻላችኋለሁ” ብለው ለማሳመን እና ደጋፊዎቻቸውንም ማክሰኞ ወጥተው ድምፅ እንዲሰጡ ለመቀስቀስ ዛሬም በተለያየ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ናቸው፡፡

ገር አቀፍ የምርጫ ድጋፍ ግምገማዎች የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደልባቸው ተናጋሪውን ቱጃር በጠባብ ድምፅ ብልጫ መምራታቸው ቀጥለዋል፡፡

አብዛኞቹ የህዝብ አስተያየት ተንታኞች ሚስስ ክሊንተን እንደሚያሸነፉ እየተነበዩ ናቸው።

ይሁን እንጂ በእነዚህ የምረጡኝ ዘመቻ የመጨረሻ ሠዓታት በተቀራረበ ድጋፍ ድምፅ እየታፋለሙ ባሉባቸውና ለወትሮ ዲሞክራቶችን በሚመርጡ አካባቢዎች ትራምፕ ከነጠቋቸው አሸንፈዋቸው ዋይት ሃውስ ሊገቡ ዕድል አላቸው።

ዶናልድ ትራምፕና ሂላሪ ክሊንተን
ዶናልድ ትራምፕና ሂላሪ ክሊንተን

የሰሞኑ ሀገር አቀፍ ግምገማ ጥንቅር ሁለት ወይም ሦስት ከመቶ የሚመሩት ክሊንተን የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው ታሪክ ሊሰሩ ይመስላል፡፡

ዋሽንግተን ፖስትና አቢስ ኒውስ ያካሄዱት የኋለኛው አብይ የድምፅ ግምገማ ደግሞ አርባ ስምንት ለአርባ ሦስት እየመሩ እንደሆነ ያሳያል።

ዛሬ የየክሊቭላንድ ካቫሊየርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን ኮከብ ተጫዋች ለብሮን ጄምስ ክሊቭላንድ ኦሃዮ ከሚሲስ ክሊንተን ጋር በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ ይቀሰቅሱላቸዋል።

ዲሞክራትዋ ዕጩ በአሁኑ ጊዜ ትራምፕ እየመሩ ያሉበትን የከባድ ፍልሚያ ክፍለ ሃገር ነጥቀው ማሸነፍ አለባቸው።

“ይሄ ምርጫ ምን ያህል ክብደት እንዳለው ሁሉም ሰው እንደሚገነዘበው ተስፋ እለኝ” ብለዋል።

ሂላሪ ክሊንተንን እንደሚደግፍ በቅርቡ በአደባባይ ያስታወቀው የብሔራዊ ቅርጫት ኳሱ ኮከብ ከወዲሁ ድምፁን መስጠቱን ገልጿል።

ዛረኢ ሚሲ ክሊንተን ወደ ኒውሃምሻየር ክፍለ ግዛትም ይጓዛሉ።

ትራምፕ ደግሞ ዛሬ በርከት ያሉ ስፍራዎች ይደርሳሉ።

በታሪክ ዲሞክራት ዕጩ በሚመርጡ በርከት ያሉ አካባቢዎች አይዋ፣ ሚኔሶታ፣ ሚሺጋን፣ ፔንሲልቬንያ እና ቨርጂኒያ ይዘዋወራሉ።

“ተቀናቃኜ የተመረጡ እንደሆን፤ ሃገሪቱ እንዴት እንደምትሆን….” ትራምፕ አጨልመው እየሳሉ ሲያሳዩ ክሊንተን በበኩላቸው

“ህብረታችን ጥንካሬችን ነው” በማለት መራጩን መቀስቀሳቸውን ቀጥለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ቅዳሜ ኔቫዳ ክፍለ ግዛት ሪኖ ከተማ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ እያሉ

“መሣሪያ የያዘ ሠው አለ” ተብሎ በተፈጠረ፣ በኋላ ግን ሀሰት ሆኖ በተገኘ ግርግር ምክንያት የደህንነት ጠባቆዎች ተሯሩጠው ከመድረኩ አፍሰው ወደ መድረኩ ጀርባ ወስደዋቸው ነበር።

አንድ ሰው ከአዳራሹ ታጅቦ ሲወሰድ የታየ ሲሆን ትረምፕ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደመድረኩ ተመልሰው ንግግራቸውን ቀጥለዋል።

ተጠርጣሪው ላይ ሽጉጥ እንዳልተገኘበት የደህንነት አገልግሎት ሠዎች መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዩሐንስ አስረስ

“ኢትዮጵያዊነትን፣ የባሕል እሴቶቻችንን የያዙ ምርቶች ለመሥራት ነው አሁን ሙሉ ጊዜዬን የሰጠሁት። ይከብዳል ግን ዓላማዬ አድርጌው ተነስቻለሁ።” የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያው ዮሃንስ አስረስ።

የጥበብ ወግ:- ከፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያው ዮሃንስ አስረስ ጋር (ክፍል አንድ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:02 0:00
የጥበብ ወግ:- ከፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያው ዮሃንስ አስረስ ጋር (ክፍል ሁለት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:12 0:00
ከበሮ - በዩሐንስ አስረስ
ከበሮ - በዩሐንስ አስረስ

ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጣ ስምንት ዓመት ሆኖታል።

Gondar, Fasiledes anicent palace
Gondar, Fasiledes anicent palace

​ከፎቶግራፍ ሥራዎቹ በተጨማሪ የኤሌክትሮኒክ የአማርኛ ፊደል መቁጠሪያና ሌሎች በፊደላት የቀለሙ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ሠርቷል። ዮሃንስ አስረስ ይባላል።

በራዲዮ መጽሔት የድምጽ መስኮት ከፎቶግራፍ ሥራዎቹ ጥቂቱን እንሰማና እናያለን።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG