በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል፡ የመድረክ አመራሮች መግለጫ ሲሰጡ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራስያዊ አንድነት መድረክ በእሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው ሕዝብ እልቂት ኃላፊነቱ የኢሕአዴግ መንግስት ነው አለ።

ገለልተኛ ዓለማአቀፍ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጠይቋል። የአደጋው መድረስ ምክንያት በሆኑት ባለሥልጣናትና የደህንነት አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ በአስችኳይ እንዲወስድ፣ ጉዳቱ ልደረሰባቸው ቤተሰቦችም ካሣና መቋቋሚያ እንዲከፍል ጠይቋል።

ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦችን እርስ በርስ ለማጋጨት እያደረገ ነው ያለው ሙከራም በህዝብ የተባበረ ትግል ይከሽፋል ብሏል።

በመግለጫው በተነሱ ጉዳዮች ከመንግስት ምላሽ ለማግኝት ያደረገነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

መለስካቸው አምሃ ዝርዝሩን ይዟል።

መድረክ በእሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው እልቂት ኃላፊነቱ የመንግስት ነው አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00

አቶ ኃይሉ ሻወል

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወል በሰማንያ ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ ያረፉት በሕክምና ሲረዱ በነበረባት ታይላንድ መሆኑን ለቪኦኤ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወልን ለሕልፈት ያበቃቸው የጤና ችግር ምን እንደሆነ ለጊዜው እያጣራን ቢሆንም እራሣቸው በፃፉት መፅሐፍ ላይ እሥር ቤት ሣሉ በገጠማቸው ቅዝቃዜ ምክንያት አከርካሪያቸው ላይ ሕመም ይሰማቸው እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታትም በብርቱ ሲታመሙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

የአቶ ኃይሉ ሻወል (ኢንጂነር)አስከሬን ነገ፤ ዓርብ አዲስ አበባ ይገባል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ባገኘን ጊዜ ይህንን ዜና እናዳብራለን፡፡ በነገ የአየር ሥርጭታችን ላይ ሥፋት ያለው ዘገባ ለማቅረብ እንጥራለን፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG