በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

“ጫካው”የስደተኞች መጠለያ መንደር

ፈረንሣይ ሰሜናዊ ግዛት ካሌይ የሚገኘውን የስደተኛ መጠለያ መንደር ማፍረስ ጀምራለች።

በመጠለያ ሰፍረው እጅግ በተጎሳቆለ ሁኔታ የሚኖሩትን ብዙ ሺህ ስደተኞች ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስፈር ትናንት ሰኞ የተጀመረው የማጓጓዝ እንቅስቃሴ ዛሬም በመቶዎች የሚቆጠሩትን አዛውሯል።

“ጫካው” ተብሎ በሚጠራው የካሌው የስደተኞች መጠለያ መንደር ከነበሩት ስደተኞች ውስጥ ወደ 2ሺህ የሚጠጉት ከ18 ዓመት በታች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን የስደተኞች ዝውውር ታዛቢ ገለጹ።

በመፍረስ ላይ ያለው “ጫካው” የስደተኞች መጠለያ መንደር
በመፍረስ ላይ ያለው “ጫካው” የስደተኞች መጠለያ መንደር

​ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

“ጫካው” የስደተኞች መጠለያ መንደር እየፈረሰ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:25 0:00

የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ሕትመት አቆመ

አዲስ ስታንዳርድ ሎጎ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥቅል ያወጣቸው መመሪያዎች የማተሚያ ቤቶችም ስጋት ሆኗል

በኢትዮጵያ የሚታተመው አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ከያዝንው የጥቅምት ወር ጀምሮ የሕትመት ስርጭቱን እንዲያቆም መገደዱን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማተሚያ ቤቶች ላይ የፈጠረው “ፍራቻና ስጋት” ለአሳታሚዎች እራስ ምታት እየሆነባቸው እንደሆነ የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ ለቪኦኤ ገልጻለች።

በአዲስ አበባ የሚታተሙ የሀገሪቱ አቢይ ጋዜጦች ህትመታቸውን ቀጥለዋል። የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማን ሔኖክ ሰማእግዜር አነጋግሯል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ሕትመት አቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG