በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በሰሜን አሜሪካ የኦሮሞ ማሕበረሰብ የተቃውሞ ሠልፍ - በዲሲ

በሠሜን አሜሪካ፣ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ የኦሮሞ ማሕበረሰብ ዛሬ ሠላማዊ ሠልፍ አድርገዋል፡፡

በዋይት ሃውስ፣ በዓለም ባንክና በዩናይትድ ስቴርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጃፍ ተካሂዷል፡፡ "በኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል፤ በዜጎች ላይ እየደረስ ያለውን እስራት፣ ግድያ እና የመብት ረገጣ እንቃወማለን" በማለትም የርሀብ አድማ አቅደዋል፡፡ በሠላማዊ ሠልፉ ላይ የነበሩ አስተያየቶቻቸውን ለቪኦኤ ሰጥተዋል፡፡

ሔኖክ ሰማእግዜር ዘግቦታል፡፡

“ዩናይትድ ስቴይትስ የሰብዓዊ መብት ለሚጥሰው የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታ ታቁም” በሰሜን አሜሪካ የኦሮሞ ማሕበረሰብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:10 0:00

በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል ተሳታፊዎች የተቃውሞ ምልክት ሲያሳዩ

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ተከትሎ እስራት መበራከቱን በዚህም ስጋት ላይ መሆናቸውን በኦሮሚያ ክልል ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከታወጀ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ይደረጉ የነበሩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መቆማቸውን፤ በከተሞቹም መረጋጋት እንዳለ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በመንግስት በኩል አስተያየት እንዲሰጡን የባለስልጣናትን ስልክ የሞከርን ሲሆን አንዳንዶቹ ስልካቸው ባለመስራቱ አንዳንዶቹ ባለመነሳቱ እንዲሁ ተነስቶ በመዘጋቱ ማንንም አግኝተን ማነጋገር ሳንችል ቀርተናል።

ጽዮን ግርማ ዘገባ አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

"በኦሮሚያ ስጋትና ፍርሃት ውስጥ ነን" - የነዋሪዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:02 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG