በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት አፍሪካ በቴክኖሎጂ አጠቃቀሟ እመርታ ልታገኝበት የምትችልበትን እድል እንደሰጣት ተነገረ።

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል የገንዘብ አቅምም ለአህጉሪቱ እንዳስገኘላት ተጠቁሟል።

የፓሪስ ስምምነት ተግባራዊ የሆነበት ፍጥነት ምክንያት የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ በጋራ ለመኖር ያለው ቁርጠኝነት መስክር ነው ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል የተከፈተው ስድስተኛው የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ ጉባዔ ዋና ርዕሱ ያደረገው

″የፓሪስ ስምምነት ለአፍሪካ ምን ይዟል?″ የሚል ነው፡፡

አዲሱ የፓሪስ ስምምነት የበካይ ጋዞችን ልቀት የመቆጣጠሪያ ስልቶችን ከመፍጠር ባሽገር ቀጣይ ልማት እንዳይቋረጥ ያረጋገጣል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አዲሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አፍሪካን በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

በኔጌሌ ቦረና ከተማና በገጠር መንደሮች ከ2መቶ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከስራ ገበታቸው ላይ ተይዘው ሲታሰሩ ከቤተስቦቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ምንጮች ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ገልፀዋል፡፡

ከታሰሩት መካከልም የመንግስት ሰራተኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንደሚገኙበት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሊባን ወረዳ ፀጥታ ቢሮ

″የታሰሩት ቦዘኔዎች ናቸው″ ይላሉ፡፡

አቶ አዶላ ሚሄሶ የሀገሪቷን ስርዓት ለማፈርሰ የጣሩ እንደማንኛውም ሰው ጉዳያቸው ተጣርቶ ለህግ ይቀረባሉ፤ ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ የፀጥታ አካሉ እየጠራ ነው ገና የሚፈለጉም ይኖራሉ ብለዋል፡፡

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG