በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International)

የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸዉን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ዓለም አቀፉ የመብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስከ ፊታችን የካቲት 9, 2008 ዓለም አቀፍ ማህበረስብ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደብዳቤ እንዲጽፍ ጥሪ አቀረበ። ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን መፍታት አለበት ሲል ጥሪ አድርጓል። የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ተማሪዎች ጋዜጠኞችና ሌሎች በኢትዮጵያ እስር ቤት ዉስጥ ስቃይ እየተፈጸመባቸዉ ነዉ የሚል ስጋቱን አሰምቷል ድርጅቱ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈዉ ህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደዉን ሰላማዊ ተቃዉሞ ለማፈን ጭካኔ የተሞለባት ግድያ፣ እስራትና ንብረት ማዉደም ፈጽሟል ይላል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ረቡዕ ባወጣዉ መግለጫ።

በሰላማዊ ተቃዉሞዉ የተካፈሉ ተማሪዎች በጭካኔ መገደላቸዉን፥ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላትና ተራ ዜጎች፥ ጋዜጠኞች ታፈሰዉ መታሰራቸዉንም ይጠቅሳል። 121 የሚደርሱ ሰዎች በመንግሥት ታጣቂዎች መገደላቸዉ በስልክ ደውለን ያገኘንው መረጃ ያስረዳ።

በቅርብ ጊዜ ከታሰሩት መካከል፣ በመንግስት ተደጋጋሚ ስቃይና እስራት የደረሰባቸዉ ድርቤ ኤርጋ የተባሉ የአንቦ ከተማ ነዋሪ የ60 ዓመት ሴት፣ የአምስት ዓመታት እስራት ፈጽመዉ በቅርቡ የተፈቱ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ፣ ነገር ኢትዮጵያ የተባለ የኢንተርኔት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ፣ የኢንተርኔት ጽሑፍ አቅራቢና የመብት ተሟጋች ዮናታን ቴሬሳ እንዲሁም የኦሮሚያ ራዲዮና ቴሌቪዢን ጋዜጠኛ ፈቃዱ ምርካና በአምነስቲ የይፈጡ ጥሪ ስማቸዉ ተጠቅሷል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአስቸኩዋይ እርምጃ ጥሪ ዓላማ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሚፈጽሙትን በደል ሕዝብ እንዲሚያዉቅ፣ የታሰሩትንም ሰዎች ስም እንደሚለይ ለማስታወስና ይህ ደግሞ ዓለም አቀፍ ሕግና የአፍሪቃ ሕብረትን የሰብአዊ መብት ሕግ የሚጥስ መሆኑን በማሳሰብ፥ ለሚፈጸመዉ በደል ተጠያቂነትና ግልጽ ምርመራ እንዲደረግ ጫና ለማድረግ ነዉ ብለዋል የድርጅቱ የመንግስታዊ ግንኙነት ዳይሬክተር አዶቴ አኩዌ።

የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃዉን የሚወስደዉ የጸረ ሽብር ሕጉን በመጥቀስ አሸባሪዎች ናቸዉ በማለት መሆኑን ጠቅሰዉ አዶቴ አኩዌ መንግስት ማናቸዉንም የሚቃወሙትን ሁሉ አሸባሪ በማለት ይፈርጃል ብለዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽና የኢትዮጵያ መንግስት ጥቃቱን እንዲያቆም ፣ የታሰሩትን እንዲፈታና የተፈጸሙትን በደሎች እንዲመረምር ዓለም አቀፍ ማህበረስብ እስከ የፊታችን የካቲት ዘጠኝ 2008 ለመንግስት ባለስልጣናት ደብዳቤ በመጻፍ ጫና እንዲያደርግ ጠይቋል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ያድምጡ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸዉን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በፍጥነት እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

የጂቡቲ ካርታ

የጂቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በዓለምአቀፍ ትብብር ቃል አቀባይ፣ ኢራን ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግዴታዎቿን ማክበር ይጠበቅባታል ሲልም መግለጫው አክሏል።

ጂቡቲ ቴህራን በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች።

ጂቡቲ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በዓለምአቀፍ ትብብር ቃል አቀባይዋ በኩል ትላንት ባወጣችው መግለጫ፥ የመንግሥቱ ቃል አቀባይ በቴህራንና በማሻድ(Mashhad) የደረሱትን ጥቃቶ በከፍተኛ ደረጃ አውግዟል ብሏል።

ኢራን ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግዴታዎቿን ማክበር ይጠበቅባታል ሲልም መግለጫው አክሏል።

በተያያዘ ዜና፥ የሱማልያ መንግሥትም ከ 20 ዓመታት የርስ በርስ ጦርነት በማገገም ላይ የምትገኘውን ሀገር ፀጥታ ለማደፍረስ ትሞክራለች ሲል በመክሰስ ከኢራን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ማቋረጡን አስታውቋል።

ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ትላንት የወጣው መግለጫም፥ ሱማእያ ተጠባባቂ አምባሳደሯን ከኢራን ጠርታለች፥ የኢራን ዲፕሎማቶችም ሱማልያን በ 72 ሰዓት ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ታዘዋል ይላል።

የኢራን ኤምባሲና ሞቃዲሾ የሚገኘው ኢማም ኮመኒ(Imam Khomeni) የተባለው የረድዔት ድርጅት ከመንግሥቱ እውቅና ውጭ፥ በየጊዜው ገጠሩን እየጎበኙ፥ በየመን፥ ሊባኖስና ኢራቅ እንደሚያደርጉት በሱማልያም ታጣቂ ቡድኖችን ለማቋቋም ሞክረዋል ሲልም መግለጫው አብራርቷል።

የሱማልያ ሠጥታ ኃይሎች ባለፈው ወር ሞቃዲሾ ውስጥ የሺሃ ሙስሊሞችን እምነት ለማስፋፋት የሞከሩ ሁለት ኢራናውያን ይዘው ማሠራቸው ይታወሳል።

ኢራን ክሱን መሠረተ ቢስ ስትል አትቀበልም።

የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ጂቡቲ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:35 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG