በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፋይል ፎቶ - በሶማልያ ክልል ድርቅ የተጠቃ አካባቢ እአአ 2016 (ሮይተርስ/REUTERS)

በኢትዮጵያ ወቅቱን ያልጠበቀ የዝናብ ስርጭትና ድርቅ፤ የግብርና ምርትን ቀንሷል፤ 10.2 ሚሊዮን ዜጎችን ለተረጂነት አጋልጧል። አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናትና እናቶች ቁጥርም በርካታ ነው።

የጋቢና ቪኦኤ ዝግጅት በድርቅ ወደ ተጠቁ አካባቢዎች ይወስደናል። ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት ለወራት የተከታተሉ ዘጋቢዎቻችን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሰባሰቧቸውን ድምጾች ይዟል።

ጉዳዩ የሚመለከተታቸውን አካላት በተለይ የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስራቸውን፣ ስኬቶችና ፈተናዎቻቸውን ከአንደበታቸው እናስደምጣችኋለን።

ሙሉ ዝግጅቱን ከድምጽ ዘገባው ተከታተሉ።

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ዝርዝር መረጃዎች በጋቢና ቪኦኤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:29:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዚካ የተባለው በሚወልዱ ህጻናት ላይ የአካል ጉድለት ያስከትላል የሚባለው ቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ በመሆኑ አራት ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

ዚካ የተባለው በሚወልዱ ህጻናት ላይ የአካል ጉድለት ያስከትላል የሚባለው ቫይረስ በመላ የአሜሪካ ሀገሮች በፍጥነት እየተዛመተ በመሆኑ አራት ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ የጤና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ማርግሬት ቻን በትንኝ የሚተላለፈው ዚካ ቫይረስ እአአ በ 1947 ዓ.ም. ለመጀምርያ ጊዜ የተገኘው ኡጋንዳ ውስት እንዳነበር ገልጸዋል። ከዚያ በኋላ በመላ አለም ተስፋድቷል።

ከቅርብ ጊዝያት ወዲህ ደግሞ ከአካላት ነርቮች ጋር እየታያያዘ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል። በሽታው የያዛቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነፍሰ-ጡር ሴቶች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆች ወልደዋል ብለዋል። እንደተወለዱ የሞቱ ህጻናትም እንዳሉ አክለውበታል።

“በአሁኑ ወቅት 23 የአሜሪካ ሀገሮችና ግዛቶች በሽታው እንደታየባቸው ቻን ገልጸዋል። የቫይረሱ መግባት በጣም ትንሽ ጭንቅላት ያላቸው ህጻናት መወለድ መብዛት ጋር ተያይዟል” ሲሉም ማርግሬት ቻን አስረድተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የዚካ በሽታ ምርመራ፣ ክትባትና ህክምና ለማቅረብ ፈጣን ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG