በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

እአአ ባለፈው ጥር ስድስት ቀን በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ እንዲቀጥል ታቅዶ የነበረው ንግግር አልተካሄደም።

በቡሩንዲያውያን መካከል የሚካሄደውን ንግግር ለማስተባበር ከደቡብ አፍሪቃ የሚቀርብ ማንኛውንም አይነት ሃሣብ በበጎ መንፈስ እንደሚቀበል የቡሩንዲ መንግስት ገልጿል።

ከደቡብ አፍሪቃ የቀረበ ኦፊሴላዊ ሃሣብ ባይኖርም ሃሣቡ ከቀረበ የሀገሪቱ መንግስት እንደሚቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሉየን ንያማትዌ (Alain Nyamitwe) ተናግረዋል።

እአአ ከ1990 ዎቹ መጨረሻ እስከ 2000 ዎቹ መጀመርያ አመታት በነበረው ጊዜ ቡሩንዲ ውስጥ በተካሄደው የሰላም ሂደት ደቡብ አፍሪቃ ወሳኝ ሚና እንደተጫወተች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

በኡጋንዳው ፕረዚዳንት ዮወሪ ሙሴቬኒ መሪነት በምስራቅ አፍሪቃ ሸምጋይነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር እስካሁን ባለው ጊዜ ውጤት አልተገኘበትም። እአአ ባለፈው ጥር ስድስት ቀን በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ እንዲቀጥል ታቅዶ የነበረው ንግግር አልተካሄደም።

ሸምጋዮቹ ቀኑን የወሰኑት ከቡሩንዲ መንግስት ጋር ሳይመካከሩ ነው በማለት የሀገሪቱ መንግስት አልተቀበለውም።

ከፍተኛው የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የተካሄደውን የምክር ቤት ምርጫ ሰርዟል። ሁለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ግን ለፕረዚዳንትነት የማጣርያ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አረጋግጧል።

የሀገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት እአአ ባለፈው ታህዝሳስ 30 ቀን የተከሄደው የመጀመርያ ዙር የምክር ቤት ምርጫ ብዙ ጉድለቶች እንደነበሩበት ገልጿል። አንዳንድ ተወዳዳሪዎች በጉዳዩ የተሳተፉ ይመስላል ሲል አክሎበታል።

በምርጫው ስለታዩ ጉድለቶች የሚገልጹ ከአራት መቶ በላይ ስሞታዎች ለምርጭ ባለስልጣኖች እንደቀርቡ የፍርድ ቤቱ ፕረዚዳንት ዛካሪ ንዱምባ (Zacharie Ndoumba) ገልጸዋል።

ኤንሰት ጆርጅስ ዶጉሌ (Anicet Georges Dologuele) እና ፋውስቲን አርቻንገ ቷደራ (Faustin Archange Touadera) የተባሉት በመጀመርያው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ተወዳዳሪዎች ግን የማጣርያ ምርጫ እንደሚያካሄዱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አረጋጋጧል። በመጀመርያው ምርጫ ውጤት መሰረት ዶጉሌ (Dologuele) 24 ከመቶ ቷደራ (Touadera) ደግሞ 19 ከመቶ ድምጽ አግኝተዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG