በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ትሪፖሊ ውስጥ የሊቢያ ወታደሮች ከጦርነት በኋላ በእረፍት ላይ (ፋይል ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

የሰላም ስምምነቱ የተደረሰው በሊቢያ ተቀናቃኝ መንግሥታት መካከል ብዙ ዙር ድርድር ከተካሄደ በኋላ መሆኑ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስተባበረውን የሊቢያ የአንድነት መንግሥት እና በተቀናቃኝ ወገኖች ባለስልጣናት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የሀገሪቱ ፓርላማ አባላት ውድቅ አደረጉት ተባለ።

የሊቢያ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ኢሳ አል አረቢ ዛሬ ሰኞ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከተገኙ እንድ መቶ አርባ አባላት መካከል ዘጠናዎቹ የአንድነት መንግሥት ካቢኔውን ውድቅ አድርገዋል ማለታቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቡዋል። በሌላ የድምጽ አሰጣጥ ደግሞ ሰማኒያ አራት የምክር ቤት አባላት የፖለቲካ ስምምነቱን ውድቅ አድርገውታል።

ባለፈው ወር በተባበሩት መንግሥታት ሸምጋይነት የተደረሰው ስምምነት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ካለው የቶብሩኩ መንግሥት እና በእስላማውያን ከሚደገፈው የትሪፖሊው መንግሥት አባላት የሚያሳትፍ የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ይጠይቃል።

ስምምነቱ የተደረሰው በሁለቱ ተቀናቃኝ መንግሥታት መካከል ብዙ ዙር ድርድር ከተካሄደ በኋላ መሆኑ ይታወሳል።

ባመንዳ፣ ካሜሩን፣ እኑጉ እና ናይጄርያ

አራት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አምስት ሰዎች መግደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ የከተማዋ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሰሜናዊ ካሜሩን የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች አዘውትረው የጥቃት ዒላማ በሚያደርጉዋት ከተማ አጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች መድረሳቸው ተገለጸ።

ቦዶ በተባለች ከተማ ዛሬ ሰኞ ማለዳ አራት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አምስት ሰዎች መግደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ የከተማዋ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሁለቱ አጥፍቶ ጠፊዎች ትልቁ የከተማዋ ዋና ገበያ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ የከተማዋ ዋናው ኬላ ላይ ማፈንዳታቸውን ዜናው አመልክቷል።

ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ ወገን የለም። ሆኖም በአካባቢው በተደጋጋሚ ጥቃቶችን ያደረሰው ቦኮ ሃራም ተጠርጥሯል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG