በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ

ከምንጊዜውም የገዘፈ በሆነው የጦርነት ስደተኞች ብዛት ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ የዓለም ሃገሮች ጥረታቸውን በዕጥፍ እንዲያሳድጉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ተማጽኖ አሰሙ።

ስዊዘርላንዱዋ ዳቮስ ከተማ እየተካሄደ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ሚስተር ኬሪ ባደረጉት ንግግር የሌሎቹንም ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሰለባዎች እንዲረዱና እየተባባሰ የመጣውን ሽብርተኝነት ከስረ መሰረቱ እንዲዋጉ ለዓለም መንግሥታቱ ተማጽኖ አቅርበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በዚህ የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. በኒው ዮርክ የዓለም የስደተኞች ቀውስን የተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ እንደሚያስተናግዱ ሚስተር ኬሪ በዓለም የኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ይፋ አድርገዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥም ንግግር አሰምተው ነበር ከዚህ በታች ካለው ቪድዮ ይመልከቱ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ በስደተኞች ቀውስ ጉዳይ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:24 0:00

ዶ/ር ፀጋዬ አራርሣ

የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉ ያስከተለው ተቃውሞን ተከትሎ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦሕዴድ ዕቅዱን መሠረዙ ይታወቃል፡፡በርካታ አድማጮች በዕቅዱና ዕቅዱን ተከትሎ በተነሣው ተቃውሞ ዙሪያ ጥያቄዎች ልከውልናል፡፡የጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ሁለት ምሑራን ጋብዟል፡፡

የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉ ያስከተለው ተቃውሞን ተከትሎ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦሕዴድ ዕቅዱን መሠረዙ ይታወቃል፡፡በርካታ አድማጮች በዕቅዱና ዕቅዱን ተከትሎ በተነሣው ተቃውሞ ዙሪያ ጥያቄዎች ልከውልናል፡፡የጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ሁለት ምሑራን ጋብዟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ልማታዊ ፖሊሲ ደጋፊ እንዲባሉ የጠየቁት አቶ ኤልያስ ግደይና በማስተር ፕላኑና በፌደራሊዝም ላይ በርካታ ጥናቶችን ያስነበቡ ዶ/ር ፀጋዬ አራርሣ ለአድማጮቻችን ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ፡፡

አዘጋጅና አቅራቢዋ ትዝታ በላቸው ነች፡፡

ሙሉውን ክፍል ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ለጥያቄዎ መልስ፡ ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ እና አቶ ኤልያስ ግደይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:50:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG