በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ - ማልታ እአአ 2014[ፋይል - ሮይተርስ]

በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ላይ የተነሣው ተቃውሞ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ የዛሬ ወር ተኩል አካባቢ አገርሽቶ እንደገና የመረጋጋት አዝማሚያ ያሳየ መስሎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ሰሞኑን ደግሞ እንደገና የመነሣሣት አዝማሚያዎች ተስተውለዋል፡፡

በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ላይ የተነሣው ተቃውሞ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ የዛሬ ወር ተኩል አካባቢ አገርሽቶ እንደገና የመረጋጋት አዝማሚያ ያሳየ መስሎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ሰሞኑን ደግሞ እንደገና የመነሣሣት አዝማሚያዎች ተስተውለዋል፡፡

ጽዮን ግርማ፣ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳና ቱጁቤ ኩሣ የአካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግረው በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሊቦ ከተማ አንድ መምህር መገደሉንና አንዲት የሰባት ዓመት ተማሪ መቁሰሏ መሰማቱን የሚናገር ዘገባ አጠናቅረዋል፤ ዝርዝሩን ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዝው ፋይል ያድምጡ፡፡

አንድ መምሕር ተገሏል፤አንዲት የሳባት ዓመት ታዳጊ መቁሰሏ ተነግሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት፤ ሐሙስ ምሽት ላይ በተጣለ አደጋ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት፤ ሐሙስ ምሽት ላይ በተጣለ አደጋ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ፡፡

በተጨማሪም ስድስት ተማሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና የአራቱ ጉዳት ከባድ መሆኑን እጅጉ ሺፈራው የሚባሉ የዲላ ከተማ የፖሊስ መኮንን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መናገራቸውን ሮይተርስ አመልክቷል፡፡

ሮይተርስ የፖሊስን መረጃ ጠቅሶ ባሠራጨው ዘገባ አደጋ ጣዮቹ የእጅ ቦምቦቹን ተማሪዎቹ ላይ ወርውረዋል፡፡

የጥቃቱ ምክንያት አልተገለፀም፤ ኃላፊነት የወሰደም ወገን የለም፡፡

እስከአሁን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሰዎች መኖራቸው ከመገለፁ ሌላ የወጣ ዝርዝር ማብራሪያ የለም፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የጌዶዖ ዞን ማዕከል የሆነችው ዲላ ከአዲስ አበባ 350 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG