በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የአል-ሸባብ ተዋጊዎች የደመሰሱት የኬኒያ ክፍለ ጦር ጥቃት እንደሚደርስ ማስጠንቀቂያ ደርሶት እንደነበር አንድ የሶማሊያ ጄነራል ተናገሩ።

ባለፈው ዓርብ ሶማሊያ ጌዶ ክፍለ ሀገር ውስጥ የአል-ሸባብ ተዋጊዎች የደመሰሱት የኬኒያ ክፍለ ጦር ጥቃት እንደሚደርስ ማስጠንቀቂያ ደርሶት እንደነበር አንድ የሶማሊያ ጄነራል ተናገሩ።

የሶማሊያ ጦር ሰራዊት የጌዶ ክፍለ ሀገር አዛዥ የሆኑት ጄነራል አባስ ኢብራሂም ጉሬይ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የኬንያው ጦር አዛዥ የመጀመሪያው ጥይት ከመተኮሱ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ሊያጠቋችሁ ነው ተብሎ ተነግሩዋቸው ነበር ብለዋል።

መረጃው ደርሶን ነግረናቸው ተዘጋጅተውበት ነበር ሲሉ ጄነራሉ አክለዋል።

ኬንያ ድንበር አጠገብ በምትገኝ የደቡባዊ ሶማሊያ ከተማ ኤል አዴ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የጦር ካምፕ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ አርባ የኬንያ ወታደሮች መገደላቸውን የጌዶ ክፍለ ሀገር ምክትል አገረ ገዢ ገልጸዋል። የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአል-ሸባብ ተዋጊዎች በኬንያ ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ማስጠንቀቂያ ደርሶ ነበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:59 0:00

የሸቭሮን ሂውስተን (Chevron Houston) ማራቶን አሽናፊዎች ከማራቶኑ ዌብ ሳይት Winners
በትላንቱ የሸቭሮን ሂውስተን (Chevron Houston) ማራቶንና አራምቾ ሂውስተን (Aramco Houston) ግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ አትሌቶች ከፍተኛ ድል ተቀዳጁ።
ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሞስነት ገረመው በግማሽ ማራቶን፥ በትልቁ ደግሞ የሴቶቹን ብሩክታይት ደገፋ፥ የወንዶቹን ጌቦ ቡርቃ፥ ግርማይ ገብሩና ብርሃኑ ደገፋ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያሉትን ከፍተኛ ሥፍራዎች ጠራርገው ወስደዋል።
በእግር ኳስ ስፖርት ዜና የአፍሪካ ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ። ፕሮግራሙን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
በትላንቱ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ አትሌቶች ከፍተኛ ድል ተቀዳጁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG