በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሰሞኑን የወጣ የአሜሪካ መንግሥት መመሪያ “እንቁላል ብሉ፤ ቡናም እስከ ስድስት ኩባያ ብትጠጡ የጤና ሥጋት ሊያድርባችሁ አይገባም”ብሏል። ለጤናዎ ያዳምጡት።

የምግብ ማስፈራሪያ እንደአሜሪካዊያን የሚወርድበት የለም ሰዉም በአብዛኛው ጠርጣራና ፈሪ ነው - ወደ አፉ በሚወስደው ላይ። በርግጥ የደፋሩም ቁጥር ጥቂት አይደለም።

የዛሬ አርባ ዓመት አካባቢ /በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1970 ዓ.ም/ የወጣ መመሪያ አሜሪካዊያን ብዙ ቅባት ወደ ሰውነታችን የሚያስገቡ ወይም በሥነ-ምግብ ባለሙያዎቹ አጠራር ኮሌስትሮል የሚያበዙ ምግቦችን ከመመገብ እንዲቆጠቡ በብርቱ ያሳስባል።

ያ መመሪያ ታዲያ በእንቁላልና መሰል በሆኑ እንዲሁም ከእንቁላል በሚሠሩ ምግቦች ምርትና ገበያ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ ቆይቷል።

የምግብ ፒራሚድ
የምግብ ፒራሚድ

ሰሞኑን ከአሜሪካ መንግሥት የሰማነው ግን የተለየ ነው። “እንቁላል ብሉ፤ ቡናም እስከ ስድስት ኩባያ ብትጠጡ የጤና ሥጋት ሊያድርባችሁ አይገባም” ብሏል።

አትብሉ ወይም ባታበዟቸው ይሻላችኋል የተባሉም አሉ፤ ደግሞም አሳምራችሁ ቀርጥፏቸው የተባሉም አሉ።

በዚሁ ዘገባ ውስጥ ስለ ልጅነት ልምሻና ስለኮሌራ ክትባቶች፤ ብዙ መድኃኒቶችን ስለለመደው ዓለምን በጭንቀት ስለዋጠው የትዩበርኩለሲስ - ቲቢ ዓይነት፤ እንዲሁም ሪፐብሊካኖቹ እንደራሴዎቹ “ሽረነዋል” ስላሉት፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደግሞ “መሻሪያችሁን ሽሬዋለሁ” ስላሉበት “ኦባማኬር” የሚል ስም ስለተሰጠው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የጤና ጥበቃ ዋስትናም የተጠናቀሩ ሪፖርቶችን ያዳምጡ።

የድምፅ ፋይሉ ተያይዟል።

የአሜሪካ አዲስ የአመጋገብ ለውጥ መመሪያ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአሜሪካ የጦር አየር ሃልይ ቢ-52 ቦምብ የሚጥሉ አውሮፕላኖች(B-52) በኦሳን የአየር ሃይል ማዕከል (Osan Air Base)እየበረሩ በፕዮንግታክ ደቡብ ኮርያ (Pyeongtaek, South Korea) እአአ 2016 (ፎቶ አሶሽየተድ ፕረስ/AP)

ደቡብ ኮሪያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኮሪያ ልሳነ ምድር መላክ ስለሚችሉ ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ስትራተጂያዊ አካላት እየተወያዩ መሆናቸውን አንድ የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣን ተናገሩ።

የአሜሪካ የአየር ጦር ሃይል ኮማንደር ሉቴነንት ጀነራል ቴረንስ (Gen. Terrence)(ግራ)እና የደቡብ ኮርያ ኮማንደር ሊዋንግ ግወን (Lee Wang-geun) በፕዮንግታክ ደቡብ ኮርያ (Pyeongtaek, South Korea) እአአ 2016 (ፎቶ አሶሽየተድ ፕረስ/AP)
የአሜሪካ የአየር ጦር ሃይል ኮማንደር ሉቴነንት ጀነራል ቴረንስ (Gen. Terrence)(ግራ)እና የደቡብ ኮርያ ኮማንደር ሊዋንግ ግወን (Lee Wang-geun) በፕዮንግታክ ደቡብ ኮርያ (Pyeongtaek, South Korea) እአአ 2016 (ፎቶ አሶሽየተድ ፕረስ/AP)

ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ላካሄደችው የኒውክሊየር መሳሪያ ሙከራ ምላሽ ለመስጠት መሆኑ በሚያስታውቅ ርምጃ ትናንት ባለረጅም ርቀት ቦምብ ጣይ ኣውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ የአየር ክልል ላይ አብርራለች።

የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኪም ሚን ሲዩክ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ሶልና ዋሽንግተን ተጨማሪ ስትራተጂያዊ ስለሚሰማሩበት መንገድ በተከታታይ እና በቅርበት እየተወያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ ልሆኑም። የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ደቡብ ኮሪያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኮሪያ ልሳነ ምድር ለመላክ የሚያስችል ስትራተጂ እየተወያዩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:52 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG