በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በሳምንታዊ ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:07 0:00

በሳምንታዊ ንግግራቸው ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ በጠበንጃ የሚፈጸም ሁከት ወረርሺኝ ለመቆጣጠር ዳር ያላደርስነው ስራ አለ በማለት ቅሬታቸውን ገለጹ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ምክር ቤት ልጆቻችንን ከጥቃት ለመጠበቅ የቻለውን ነገር ቢያደርግስ? በማለት “በሀገራችን በጠበንጃ የሚፈጸም ሁከት ወረርሺኝ ለመቆጣጠር ዳር ያላደርስነው ስራ” ባሉት ያላቸውን ብስጭት በሳምንታዊ ንግግራቸው ላይ ገለጹ።

ባራክ ኦባማ ሁሉን የሁከት ተግባር ልናቆም አንችልም፣ ግን አንድ እንኩዋን ለማስቆም ብንሞክርስ ምን አለ? በማለት የሀገሪቱ ምክር ቤት ምንም ዓይነት ርምጃ ለመውሰድ ወረርሺኙን ለመቀነስ በተደጋጋሚ ሳይችል መቅረቱን አመልክትዋል።

ከሶስት ዓመታት በፊት በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የቀረበው “Commonsense Bill” የተባለው ህግ መሳሪያ የሚገዛ ማናቸውም ሰው የግል ታሪኩ እንዲመረመር የሚያደርግ እና ሰማኒያ ከመቶው ኣሜሪካዊ የሚደግፈው እንደነበር አውስተዋል።

የብሔራዊ የ ጠመንጃ ባለቤትነት ማህበር (National Rifle Association) አብዛኞቹ አባላት የሚደግፉት እንደነበርና ያስታወሱት ፕሬዚደንቱ ሆኖም መሳሪያ ሻጭ ሎቢዪስቶች የተቃውሞ ዘመቻ እንዳካሄዱበትና የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ህጉን እንዳያልፍ እንዳከላከልው አስረድተዋል።

ባለስልጣኖቻቸው በመሳሪያ የሚፈጸም ሁከት ተግባር እንዲቀነስ የሚያስችል ኣዲስ ርምጃ እንዲያጠኑ አዝዣለሁ ያሉት ፕሬዚደንቱ የፊታችን ሰኞ ከጠቅላይ አቃቤ ህጋቸው ሎሬታ ሊንች ጋር እንደሚወያዩበት አስታውቀዋል።

መረራ ጉዲና በኦሮምያ ክልል ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ የመድረክ ተሳታፊዎች ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ የተነሳ ፎቶ እአአ 2010 [ፋይል ፎቶ ሮይተርስ]

መንግስት በኛ ድርጅት ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ የሚያስችሉትን እርምጃዎች እየወሰደ ነው ሲሉም የኦፌኮ ሊቀ-መንበር ዶክተር መራራ ጉዲና ተናግረዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሃፊ አቶ በቀለ ነጋ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል። ተንቀሳቃሽ ስልካቸውንም ተነጥቀዋል ሲሉ የፓርቲው ሊቀ-መንበር አስታወቁ።

መንግስት በኛ ድርጅት ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ የሚያስችሉትን እርምጃዎች እየወሰደ ነው ሲሉም የኦፌኮ ሊቀ-መንበር ዶክተር መራራ ጉዲና ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ጭምር ሁከት እንዳስነሱና እንደመሩ ማስረጃ አለን ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን መናገራቸው ይታወቃል።

ዘጋብያችን እስክንደር ፍሬው ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን አጠናቅሮ አቅርቦታል። ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሃፊ አቶ በቀለ ነጋ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG