በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፋይል ፎቶ [አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

ዝናቡ በመቅረቱ የተዘራው ጤፍም ሆነ ስንዴ ምርት አለማፍራቱን የምዕራብ አርሲ አርሦ አደሮች ገልፀዋል።

የተዘራው ሁሉ መጥፋቱን ለቪኦኤ የገለፁ አንድ የምዕራብ አርሲ አርሦ አደር የሰሞኑ እርጥበት ሊያበቅልልን ይችላል በሚል ተስፋ ያደረ መሬት ለማረስና ለመዝራት እየሞከሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“ሰዉ ስለ ድርቅና ስለ መራቡ መናገር ይፈራል” ያሉት እኒሁ አርሦ አደር “ስለረሃቡ ይደብቃሉ፤ በፍፁም አይናገሩም፤ ስለ ረሃብ የተናገረ ሰው፤ ሰው እንደገደለ ተደርጎ ይታያል፤ ያስራሉ፣ ይደበድባሉ፤ ሕዝቡንም ያስፈራራሉ” ሲሉ ከስሰዋል፡፡

በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው መኖሩን ባያውቁም ብርቱ ረሃብ እንዳለ የተናገሩት እኒሁ አርሦ አደር በገበሬው ውስጥ የተሠማሩት የልማት ሠራተኞችም የውሸት ዘገባ እንደሚያስተላልፉና፤ የምግብ ዕጥረት፣ ድርቅና ረሃብ መኖሩን እንደማይናገሩ ጠቁመዋል፡፡

እነዚህን ክሦች አስተባብለው ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የምዕራብ አርሲ አስተዳዳሪ አቶ አባድር አብዳ መንግሥት “የአንድም ሰው ሕይወት መጥፋት የለበትም የሚል ፖሊሲ ይዞ እየሠራ ነው” ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቀበሌዎች ከዚህ ቀደምም በእርዳታ ታቅፈው ሲረዱ መቆየታቸውንና አሁንም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር አለመፈጠሩን አስተዳዳሪው አቶ አባድር አብዳ አመልክተዋል፡፡ ዘገባውን ለማዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የድርቁ ገፅታ በምዕራብ አርሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:46 0:00

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ ክፍሎችና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለተቀሰቀሰው ሁከት መንስዔ ነው ብሏል።

የከሠሩ የፖለቲካ ኃይሎችና በአሸባሪነት የተፈረጁ ድርጅቶች ያሠራጩት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ ክፍሎችና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለተቀሰቀሰው ሁከት መንስዔ ነው ሲል የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከጀርባ አሉ የተባሉትን ኃይሎች ማንነት መግለጫው በዝርዝር አልገለፀም፡፡ በተፈጠረው ሁከትም ሦስት ወጣቶች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሺነር ይፋ አድርገው ኅብረተሰቡን እያደናገሩ ናቸው ያሏቸውን አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

መለስካቸው አምሃ ተጨማሪ ዝርዝር ልኳል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሚያ ለተቀሰቀሰው ሁከት መንስዔ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG