በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

መድረክ ሰልፉን አዛወረ

መድረክ

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችንና የተፈፀሙ ግድያዎችን ለማውገዝ በሚል ለዛሬ ጠርቶት የነበረ ሰልፍ ዕውቅና ባለማግኘቱ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን መድረክ አስታውቋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:01:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችንና የተፈፀሙ ግድያዎችን ለማውገዝ በሚል ለዛሬ ጠርቶት የነበረ ሰልፍ ዕውቅና ባለማግኘቱ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን መድረክ አስታውቋል፡፡

መድረክ ትናንት ባካሄደው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስብሰባ ነው ውሣኔውን ያሳለፈው፡፡

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰጡት መግለጫ የሰልፉ ዓላማ ሲያብራሩ ሕገወጥ ግድያዎችንና ሕገ መንግሥታዊ የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግን ነፃነት በመፃረር የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችን ለመኮነን እና ለዚህም ለተሰዉት ወገኖቻችን ያለንን ክብር ለመግለፅ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሰልፉ ዕውቅና እንዳይሰጥ ያደረጉትን ምክንያቶች ሲዘረዝር “ሰልፉ የሚያልፍባቸው አካባቢዎች በልማት ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ያለባቸውና በርካታ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት የሚገኙባቸው መሆናቸውን ገልፆ “እንዲሁም አሁን ባለው የወቅቱ ሁኔታም ጥያቄውን ተቀብለን ዕውቅና ለመስጠት እንቸገራለን” ብሏል፡፡

መድረክ ሰልፉን ለመቼ እንዳሰበ አልተገለፀም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ራዕይ ከፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ወጣ

ራዕይ ፓርቲ የኅዳሴ ግድብ ግንባታን እንደሚደግፍ አስታወቀ

ኢሕአደግን ጨምሮ ዘጠኝ ፓርቲዎች አባል ከሆኑበት አገርአቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ራሱን ማግለሉን ራዕይ ፓርቲ አስታወቀ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢሕአደግን ጨምሮ ዘጠኝ ፓርቲዎች አባል ከሆኑበት አገርአቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ራሱን ማግለሉን ራዕይ ፓርቲ አስታወቀ።

“ምክር ቤቱ እየሠራ ያለው በምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጁና በአገርአቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት አይደለም” ይላል ፓርቲው።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ባለው የተቃውሞ እንቅስቃሴና በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ፓርቲው በማሳያነት ጠቅሷል።

የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ ተሻለ ሰብሮን ያነጋገረውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG