በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ኾነው ሠርተዋል።

አሁን ደግሞ በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየታየ ያለውን ያለመረጋጋት የቀሰቀሰው ተቃውሞ የሽብር አድራጎት ሳይሆን በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተፈቀደ፣ መዘዞቹ ደግሞ በሕግ አግባብ ሊታዩ የሚችል የተቃውሞ አቀራረብና መብትም ነው ሲሉ የሕግ አስተማሪና ተመራማሪው አቶ ፀጋዬ ረጋሳ ሃራርሳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡

ጽዮን ግርማ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳን አነጋግራቸዋለች፡፡

የመጀመሪያውን ክፍል ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ(ክፍል አንድ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]

ውጭ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ።

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለሥልጣናት መግለጫ ሰጥተዋል።

የኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫና ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሁከቱን ከበስተጀርባ ሆነው እያቀጣጠሉ ያሉት፥ በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱና በውጭ ባሸባሪነት የተፈረጁ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።

በኮሚኒኬሽንስ ሚኒስትሩ ስለተሰጡ አስተያየቶች መልስ እንዲሰጡ፥ ለዛሬ በውጭ ያለውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስን ጋብዘናል።

ሰሎሞን ክፍሌ ነው ያነጋገራቸው ያጠናቀረውን ዘገባ ለማዳመት ከዚህ በታች ያለውን የድምች ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ቃለ-ምልልስ ከየኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:24 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG