በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

እነ አቶ መላኩ ፋንታ ዶሴ ተቀጠረ

ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች ተከሣሾች ያቀረቧቸውን የክሥ መቃወሚያዎች በአብዛኛው ውድቅ አድርጓል፡፡

በፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሠረት አቃቢ ሕግ የሚያሻሽላቸውን ክሦች የሚያቀርብበትን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ለዝርዝሩ የፍርድ ቤቱን ውሎ የተከታተለውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
አቶ በቀለ ነጋ - የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ


please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ነቀምቴና ሃረማያን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሎች ትናንትና ዛሬ በሰዉ ላይ ድብደባና እሥራት እየፈፀሙ ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ተናግረዋል፡፡

አቶ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ በምዕራብ ሸዋ በግንደበረትና ጀልዱ፤ እንዲሁም ምሥራቅ ሸዋ አርሲ ነገሌ ተማሪዎች እየተያዙ መታሠራቸውን በወለጋ፤ ነቀምቴም ብዙ ሰው እየተያዘ መታሠሩን ገልፀዋል፡፡

ትናንት ደግሞ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ አሥር ተማሪዎች ከየማደሪያቸው በፖሊሶች መወሰዳቸውን አቶ በቀለ አክለው ገልፀዋል፡፡

ፓርቲያቸው ሁኔታውን ለመንግሥት ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ከመንግሥት አካላት ስለጉዳዩ ማብራሪያ ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢደረጉም ለጊዜው አልተሣካም፤ ምላሽ በተገኘ ጊዜ እናወጣለን፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG