በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዜና ዕረፍት

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

ባልደረባችን ሰሎሞን ክፍሌ ባለቤቱን አጥቷል፡፡

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሰሎሞን ክፍሌ ባለቤት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ያረፈችው በጠና ታምማ ላለፉት ሦስት ወራት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል በሕክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ ነው፡፡

ወ/ሮ ገነት ያረፈችው በቅርብ ሲንከባከቧት በነበሩት ባለቤቷ፣ ልጅዋ እናቷ፣ አክስቷና ሌሎችም የቤተሰብ አባላትና የቤተሰቡ ወዳጆች በተገኙበት ነው፡፡

ወ/ሮ ገነት ዘውዴና አቶ ሰሎሞን ክፍሌ በረዥሙ የትዳር ዘመናቸው አንዲት ልጅ አፍርተዋል፡፡
ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ቤተሰቦች አርሊንግተን ቨርጂንያ፤ ኮሎምቢያ ፓይክ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አዳራሽ ውስጥ ዘመድ ወዳጅን እያስተናገዱ ሲሆን የፊታችን ሐሙስ፤ አፕሪል 3/2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ በምትገኘው ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኖ አስከሬኑ ወደ ትውልድ ሃገሯ ኢትዮጵያ በዚያው የሚሸኝ መሆኑን የቤተሰቡ አባላት ገልፀዋል፡፡

የቪኦኤ ባልደረቦች በተወዳጅዋ ጓደኛችን ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ዕረፍት በእጅጉ አዝነናል፤ ለመላ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ትብብር ሃገሮች

ኤርትራ የጣልቃገብነትን ክሥ አስተባበለች፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


“የኤርትራ መንግሥት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጁን እያስገባ ነው” ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠቡት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ “ግጭቱን በማባባስ በኩል የኤርትራ መንግሥት የገባበት ሁኔታ አለ” ብለዋል፡፡

ኤርትራ ከደቡብ ሱዳን ሕዝብና መንግሥት ጋር ያላት ገንቢ ግንኙነት መሆኑን በመጠቆም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤርትራ ላይ አበሣጭ የሆኑ ውሸቶች ይነገራሉ ክሱን አስተባብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ሱዳን የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ አምባሣደር ዶናልድ ቡዝ ከላይ የተጠቀሱት ክሦች መንግሥታቸው ከብዙ የአካባቢው ሃገሮች የደረሰው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG