በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዓለም ፀረ-ኤድስ ዘመቻ ቀን

ኢትዮጵያ 26ኛውን የዓለም የኤድስ ቀን ጋምቤላ ከተማ ላይ ትናንት በተካሄደ ይፋ ሥነ-ሥርዓት አስባለች፡፡

የዓለም የኤድስ ቀን
የዓለም የኤድስ ቀን

please wait

No media source currently available

0:00 0:23:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያ 26ኛውን የዓለም የኤድስ ቀን ጋምቤላ ከተማ ላይ ትናንት በተካሄደ ይፋ ሥነ-ሥርዓት አስባለች፡፡

የኤችአይቪ ሥርጭት መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ 1 ነጥብ 2 ከመቶ ሲሆን የጋምቤላ ሥርጭት መጠን ግን 5 ነጥብ 8 መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኘው ሰው ቁጥር ከ750 ሺህ እስከ 800 ሺህ እንደሚደርስም ተነግሯል፡፡

የዓመቱ የኤድስ ቀን መሪ ቃል “አንድም ሰው በኤችአይቪ እንዳይያዝ፣ እንዳይገለል እና እንዳይሞት ኃላፊነታችንን እንወጣ” የሚል ነው፡፡

ኤችአይቪ ዓለምአቀፍ ወረርሽኝ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ባለፈው ወደ አርባ ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ወደ ሰማንያ ሚሊየን ሰው ለኤችአይቪ የተጋለጠ ሲሆን ከመካከሉም ግማሽ ያህሉ በኤድስ ምክንያት አልፏል፡፡

ዓለም ዛሬ “ዘመቻ ዜሮ”ን እያካሄደ ሲሆን በመጭዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ ኤድስን ለማቆም እየተንቀሣቀሰ ይገኛል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ፎቶ ፋይል /ይህ ፎቶ የተገኘው ከአንድ የታንዛኒያ ዌብ ሣይት ነው፡፡ በሕገወጥ አሸሸጋጋሪዎች በብረት ኮንቴይነር ታጭቀው ሲወሰዱ የፀጥታ ኃይሎች የያዟቸውን “ኢትዮጵያዊያን” ነው የሚያሣየው፡፡ ከዚህ ታሪክ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው በዚህ ፎቶ ግራፍ ውስጥ ለመኖሩ እርግጠኞች አይደለንም፡፡/

በሕገወጥ መንገድ ተታልለው ከሃገር ከወጡ በኋላ በታንዛኒያ እሥር ቤቶች ውስጥ ቆይተው እንደነበር የገለፃቸውን 435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡

ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው የፕሬስ መግለጫ
ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው የፕሬስ መግለጫ

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በሕገወጥ መንገድ ተታልለው ከሃገር ከወጡ በኋላ በታንዛኒያ እሥር ቤቶች ውስጥ ቆይተው እንደነበር የገለፃቸውን 435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡

ናይሮቢ በሚገኘው በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ካውንስለር አቶ መለስ ዓለም ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ መሠረት የመጀመሪያው ቡድን አባላት የሆኑት 253 ተመላሾች ዛሬ፤ ዓርብ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ወደሃገራቸው እየተመለሱ ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የታንዛኒያ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና አዲስ አበባ የሚገኘው የዓለምአቀፉ የፍልሰት ጉዳዮች - አይኦኤም የኢትዮጵያ ቢሮ በጋራ ባደረጉት ጥረት መሆኑን የኤምባሲው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ኬንያ የሚገኘውና ታንዛኒያን ጨምሮ ሌሎችንም የአካባቢውን ሃገሮች የሚሸፍነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ታንዛኒያ ሄደው የዜግነት ማጣራት ማድረጋቸውንና ኢትዮጵያዊያኑ የአንድ ዓመት የእሥር ጊዜያቸውን የጨረሱ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ ያልቀረቡ፣ ገሚሶቹም የፍርድ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በተደረገ ጥረት በታንዛኒያ መንግሥት ምኅረት የተደረገላቸው መሆናቸውን መግለጫው ጠቁሟል፡፡

ዕድሜአቸው ከ15 እስከ 39 ዓመት የሆነና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሃድያ እና ሆሣዕና አካባቢ የመጡት ኢትዮጵያዊያን እንደገለፁት ከእነርሱ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በሚል ከተነሱ ውስጥ መንገድ ላይ ሕይወታቸው ያለፈና አካላቸው የጎደለ ብዙዎች እንዳሉ መናገራቸውን ኤምባሲው በዚሁ መግለጫው ላይ አስፍሯል፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ከሃገር ለመውጣት ከ50 ሺህ እስከ 70 ሺህ ብር ለሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ መክፈላቸውን እንደገለፁለት ኤምባሲው ጠቁሟል፡፡

አቶ መለስ ዓለም ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ለመስማት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ይክፈቱ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG