በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አይ.ቲ.ኤስ-ኢትዮጵያ

የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ሃገሮች ለምጣኔ ኃብት እድገትና የባሕል መጋራት እንደ ድልድይ የሚጠቀሙበት የዕድገት አቀጣጣይ ዘዴ ነው፡፡ትራንስፖርት
ትራንስፖርት

please wait

No media source currently available

0:00 0:15:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ሃገሮች ለምጣኔ ኃብት እድገትና የባሕል መጋራት እንደ ድልድይ የሚጠቀሙበት የዕድገት አቀጣጣይ ዘዴ ነው፡፡

በሣይንስና ሕይወት ዝግጅት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሣለጥ ይረዳል ያሉትን ዘዴ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መዝለቃቸውን አንድ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ያጫውቱናል፡፡

አቶ አብዩ ብርሌ ይባላሉ፤ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ባለድርሻ የሚባሉ አካላት ስለፈጠሩትና እርሣቸው በአማካሪነት እያገለገሉት ስላሉት አይ.ቲ.ኤስ-ኢትዮጵያ ስለሚባል ኅብረት ሥራም ይነግሩናል፡፡
ትራንስፖርት
ትራንስፖርት

ትራንስፖርት የማንኛውም ሃገር ቁልፍ መሠረተ-ልማት ነው፤ ያለትራንስፖርት ዘዴ በየትኛውም ዘመንና የዕድገት ደረጃው ቢሆን የሰው ልጅ ሕይወት ሂደትና መስተጋብር አይታሰብም፡፡ በተለይ በያዝነው የተጣደፈና የተራቀቀ ዘመን …

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የኢትዮጵያ ወታደሮች አሚሶምን ተቀላቀሉ /ፎቶ - ፋይል/ሞንታዥ/

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሶማሊያ ውስጥ ከሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል - አሚሶም ጋር በይፋ ተቀላቀሉ፡፡
ኮ/ል አሊ አደን ሁማድ - የአሚሶም ቃልአቀባይ
ኮ/ል አሊ አደን ሁማድ - የአሚሶም ቃልአቀባይ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሶማሊያ ውስጥ ከሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል - አሚሶም ጋር በይፋ ተቀላቀሉ፡፡

የኢትዮጵያ ከአሚሶም ጋር መቀላቀል ከአል-ሻባብ ጋር እየተፋለመ ላለው ኃይል ተጨማሪ አቅም ይሰጠዋል ተብሏል፡፡

ቀደም ባለው ጊዜም የአፍሪካው ሰላም ጥበቃ ጦር አካል አይሁኑ እንጂ የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች በምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉ አካባቢዎችን ከአል-ሻባብ ነፃ አድርገው በመቆጣጠር ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ይታወቃል፡፡

አምባሣደር ዴቪድ ሺን
አምባሣደር ዴቪድ ሺን
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረትን ኃይል መቀላቀል ለአል-ሻባብ ማንሠራራት ዕድል ሊከፍት ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው በአካባቢው ላይ ሰፊ ዕውቀት ያላቸው አምባሣደር ዴቪድ ሺን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG