በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኢህአዲግ የቀድሞውን ወታደራዊ መንግስት አውርዶ የሥልጣኑን መንበር የተረከበበት ግንቦት 20 እነሆ ዛሬ 20 ዓመት ሞላው።

ለተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማስመዝገቡን ያስታወቀበትን ጨምሮ «የኅዝቡን ህይወት ለማሻሻል ያስቻሉ በርካታ ውጥኖች አሳክቻለሁ፤» ሲል፤ በአንፃሩ በተቃዋሚው ጎራ ተሰልፈው በአገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በበኩላቸው «የአንድ ፓርቲ የበላይነትና የአንድ መሪ አምባገነንነት ወደ ሰፈነበት የከፋ አዝማሚያ እያመራን ነው፤» ሲሉ ይኮንናሉ።

ሁለት የተቃዋሚ መሪዎች የዛሬውን ግንቦት 20 የኢህአዴግን ሃያኛ ዓመት የሥልጣን ቆይታ እንደየፖለቲካ አቋማቸው የቃኙበትን ዘገባ ቀጥሎ ያድምጡ።

«መንግስት የገባውን ውል አፈረሰ፤» ይላል የፅሁፋቸው ርዕስ። የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች በአገር ውስጥ «ሊሰማሩበት አይችሉም፤» መባሉ አነጋጋሪ የሆነበትን አንድ የሥራ መስክ ይመለከታል።

ሙልጌታ አረጋዊ አረጋዊ ይባላሉ። ቀደም ሲል በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅና ሞያ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱበት ካለፈው ዓመት አንስቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የኅገ-መንግስት እና የመገናኛ ብዙኃን ህግ ትምህርቶች መምህር ናቸው።

በሌሎች የተለያዩ የሥራ መስኮች ዙሪያ የሚነሱ መሰል ጥያቄዎችም በተለያዩ ጊዜያት ይሰማሉ። አቶ ሙልጌታ አዲስ አበባ ውስጥ በሚታተም አንድ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ለንባብ ያበቁትን ፅሁፍ መነሻ ያደረገ ቃለ ምልልስ በተለይ በጥብቅና ሞያ ላይ ያተኩራል።

የመጀመሪያውን ክፍል ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ፤

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG