በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

መንግስት በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ያወጣው የዋጋ ተመን ለስኳርና ዘይት እጥረት ምክንያት ነዉ ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የስኳርና ዘይት እጥረት በተለይ በችርቻሮ ሱቆች አካባቢ በግልጽ ይታያል። በየቀበሌው የተቋቋሙት የሸማቾች ማህበራት ስኳርና ዘይት የመሳሰሉ ሸቀጦችን ከመንግስት በመረከብ ሲሸጡ ቆይተዋል፣ ሆኖም ይህም ችግሩ አልፈታም።

እጥረቱ የተከሰተው ላለፉት ሁለት ወራት መሆኑንና የሚመቁሙ ቸርቻሪዎች አሰራሩ እነርሱን ያገለለ መሆኑን ይናገራሉ። የዚህ ችግር መነሻም መንግስት በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ያወጣው የዋጋ ተመን ነው ይላሉ። በተለይም ዘጋቢአችን እስክንድር ፍሬውን ያነጋገረ ወጣት ባለሱቅ ”አስመጪዎች ስራቸው አትርፈው መነገድ መሆኑ ሲታወቅ፣ ትርፍ ካላገኙ ግን መሸጥ አይችሉም።

መንግስት በተለይ የዘይት ዋጋ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ነበር ያደረገዉ። በተለይ ተመን ወጥቶ የሸማቾች ህብረት ዘይትና ስኳር ማከፋፈል ከጀመሩ ወዲህ ገበያው ሊረጋጋ አልቻለም፣ ተመን ባይጣልና አስመጪዎች ቢያከፋፍሉ ኖሮ ዋጋው ቢወደድም ነጋዴዎች በመጠነኛ ትርፍ ይሸጡ ነበር፣ ዋጋውም ይረጋጋ ነበር” ሲል አብራርቶአል።

በአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን የተነበበው የመንግስት መግለጫ ግን መንግስት መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ዘይት ወደ አገር ማስገባቱን ገልጾአል። ቀደም ሲል የነበረውን አሰራር በመቀየርም ዘይት በችርቻሮ ሱቆች ጭምር እንዲገኝ እንደሚደረግም አስታውቋል። ከመንግስት ጅምላ በመውሰድ ለሱቆቹ የሚያከፋፍሉት ደግሞ የሱቆች ማህበራት ናቸው ተብሎአል። ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን በ1995 ዓ.ም. ማመልከቻ ካስገባች ወዲህ፤ የአለም መንግስታት የገበያ ጉዳያቸውን የሚፈቱበትን የጋራ ማህበር ለመቀላቀል በመጠባበቅ ትገኛለች።

ይሄም የሆነው ለዘመናት የሀገር ውስጥ የኢኖኖሚ ተቋሞቿን በተለይ ኢንዱስትሪዎቿል ስታጥናክር የቆየችው ቻይና የWTO አባል በሆነች በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ነው።

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ድሃ አገሮች የ WTO አባል መሆናቸው ለህዝባቸውና ለወደፊት እድገታቸውም ምን አይነት ጥቅም ያስገኛል? መንግስቱ በኢኮኖሚው የሚያስገባው ጣልቃ-ገብነትስ ወደፊት ከአባልነቱ ጋር እንዴት አብሮ ይሄዳል?

የንግድና ምጣኔ ሀብት አዘጋጅ ሔኖክ ሰማእግዜር በአዳማ ዪኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ አስተማሪ የሆነውን አቶ ኢዮብ ሀይሌ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ስቱዲዮአችን ለውይይት ጋብዞት ነበር።

ውይይቱን ያዳምጡ

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG