በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዲቪ ውጤት ተሠረዘ

ባለፈው ሣምንት ይፋ የተደረገው የዲቪ ዕድለኞች ዝርዝር መሠረዙን የአሜሪካ ኤምባሲ ኮንሱላር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2003 ዓ.ም ይፋ እንደተደረገው አአአ ለ2012 ዓ.ም ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (ዲቪ ሎተሪ) አመልክተው ከነበሩ መካከል ዕድሉን አግኝታችኋል ተብለው ዝርዝራቸው ባለፈው ሣምንት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዌብ ሣይት ላይ የወጣው በሙሉ ተሠርዟል፡፡

ውጤቱ ውድቅ የተደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ በሚያዘው መሠረት ማመልከቻዎቹ “በዘፈደ የመረጣ ዘዴ ስላልተስተናገዱ ነው” ተብሏል፡፡

ባለሥልጣናቱ ጨምረው እንዳስረዱት አመልካቾች አዲሱን ውጤት ከሐምሌ 8 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

ባለታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ መትተዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ተሳፋሪዎችን የሚያመላልሱ (በልማድ ሚኒባስ በመባል የሚታወቁት) ታክሲዎች በተመደበላቸው መስመር ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው የታክሲ አሰራር ሰሞኑን ተግባራዊ ቢደረግም ከቅሬታዎች ነፃ አልሆነም።

ሠሞኑን በከተማይቱ ታዬ የሚባለው የተሽከርካሪ እጥረት እያነጋገረ ባለበት፤ ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች፥ ተሳፋሪውንና አስከርካሪዎችን በማነጋገርና እንዲሁም የታክሲ ባለንብረቶችንና አዲሱን ህግ ያረቀቀና ተግባራዊነቱን የሚከታተለውን የመንግስት ተቋም ተጠሪ ጨምሮ የሁሉንም ወገኖች ዕይታ ያካተተ ሠፋ ያለ ዘገባ አጠናቅረዋል።

ሰኞለት ሥራ አቁመው የነበሩት ሚኒባስ ታክሲዎች በአብዛኛው ዛሬ ወደ ሥራ እንደተመለሱ የአዲስ አበባ ትራንስፖርትና መንገዶች ቢሮ ባለሥልጣን ሲገልፁ፤ የታክሲ ባለቤቶች ደግሞ አሁንም አሉን የሚሏቸውን ልዩ ልዩ ችግሮች ይዘረዝራሉ።

ዘጋቢዎቻችን እስክንድር ፍሬውና መለስካቸው አምሃ ያጠናቀሩትን ዘገባ ያዳምጡ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG