በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያንና ኤርትራን መንግሥታት በመብቶች ረገጣ ከሰሰ፡፡

"በኢትዮጵያ ገዢው የሕዝባዊ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ያለፈውን ዓመት ግንቦት ምርጫ ያሸነፈው በማስፈራራት፣ በነፃ የመሰብሰብ ወይም በማኅበር የመደራጀት መብቶችን በመገደብ፣ ሰብዓዊ መብቶችንና የነፃውን ፕሬስ እንቅስቃሴዎች አብዝተው የሚገድቡ ሕጎች ተግባራዊ በሆኑበት፥ የሀገሪቱን የኃብት ምንጮችና ከውጭ የሚገኝ ዕርዳታንና የሥራ ዕድሎችን በስፋት ሕዝቡን ለመቆጣጠሪያነት በመጠቀም ነው" ሲል የመብቶችና የነፃነት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ አስታውቋል።

በኤርትራም መንግሥቱ የሕዝቡን ሃሣብን የመግለፅ እና የሐይማኖት ነፃነቶችን በብርቱ መገደቡን፣ በሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ፥ ነፃ ሚዲያም ሆነ ሲቪክ ማኅበራትን ማቋቋም የተከለከለ መሆኑን ገልጿል። በኤርትራ ወታደራዊ ምልመላ ግዴታ መሆኑንና በምልመላው መሣተፍ ያልፈለጉ ግለሰቦችንና ቤተሰቦቻቸውን መንግሥቱ እንደሚያስር የአምነስቲ ሪፖርት አስታውቋል።

ማንኛውም ኤርትራዊ ድንበር አቋርጦ ለማምለጥ ከሞከረ እንዲገደል የተሰጠው ትዕዛዝ አሁንም በሥራ ላይ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አክሎ አስታውቋል።

ሰሎሞን ክፍሌ በለንደን የኢትዮጵያና ኤርትራን ጉዳይ የሚከታተሉትን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዴስክ ኃላፊ ክሌይር ቤስቶንን አነጋግሯል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

የግብፅ የተቀየረ አቋም

በአባይ ወንዝ ዓለምአቀፍ ግንኙነት ላይ የአዲሲቱ ግብፅ አቋም የመለሣለስ አዝማሚያ ያሣየ ይመስላል፡፡

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ያጠናቀቁት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በአባይ ውኃ መጋራት ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ጭቅጭቅ ለመፍታት በራሳቸው ቃል "አዲስ ሁኔታ ከፍቷል" ሲሉ አስታውቀዋል።

በዩጋንዳና በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ የግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሣም ሻራፍ የሙባረክ አስተዳደር የሚገለፅበት በግብፅና በጥቁር አፍሪካ መካከል ያለው ውጥረት እየረገበ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡

"እኛ እኮ እራሣችንም አፍሪካዊያን ነን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሻራፍ፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG