በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በዓባይ ወንዝ ላይ የሚሰራዉ ግድብ፣ በወንዙ ተፋሰስ ላይ ከሚሰሩ የልማት ስራዎች የመጀመሪያዉ እንደሆነ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ስርዓቱንና ሌሎች ለዉጦችን በማድረግ በአባይ ልማት ተሳትፎ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ

”የዉሃ ሃብታችን ትዉልዱና የዩኒቨርሲቲዉ ሚና በሚል ርእስ በተዘጋጀ አዉደ ጥናት ላይ ሁለት የመንግስት ባለሥልጣናት የመክፈቻ ንግግር አድርገዉ ነበረ። የዉሃና ኤነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለምአየሁ ተገኑ በአዉደ ጥናቱ መክፈቻ ንግግራቸዉ፣ በዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የሚከናወኑ ሥራዎች አንዳቸዉም የተፋሰሱ ግርጌ አገሮችን አይጎዱም ብለዋል።

በዓባይ ወንዝ ላይ በህዳሴ ግድብ የተጀመረዉ የልማት ዉጥን የመጀመሪዉ እንጂ የመጨረሻዉ አይደለም፣ በርካታ የልማት ሥራዎች ከፊታችን ይጠብቁናል ብለዋል። የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጁነዲን ሳዶ ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዓባይ ተፋሰስ ልማትም ሆነ በሌሎች የአገሪቱ ልማት ሥራዎች እንደ አንድ አንጋፋ የትምህርት ተቋም በብቃት ለመሳተፍ በተቋሙ ዉስጥ መካሄድ ይገባቸዋል ስላሉት ለዉጦች ተናግረዋል። በእርሳቸዉ አገላለጽ እስካሁን በአገሪቱ ዉስጥ ተከናዉነዋል ባሉዋቸዉ የልማት ሥራዎች ዩነቨርሲቲዉ ያበረከተዉ በቂ አይደለም።

የዩኒቨርሲቲ እንዱስትሪ ትስስሩ ከሥር ጀምሮ መቀየር አለበት። ከካሪኩለም ቀረጻና ከፖሊሲ አቅጣጫ ጀምሮ፣ በመቀየር ምሁራኖቻችንና ተማሪዎቻችን ከተጨባጭ ሥራ ጋር መገናኘት አለባቸዉ ብለዋል። ለዝርዝሩ መለስካቸዉ አመሃ ከአዲስ አበባ የላከዉን ዘገባ ያድምጡ።

ባለፉት ስድስት ወራት የደረሰው የዝናብ እጥረት ሁኔታውን እንዳባባሰ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት ወር የምግብ እርዳታ የጠየቀችው 2.8 ለሚሆኑ ሰዎች ነብር። ይህም ባለፉት አመታት ከነብረው ያነሰ ነው። ይሁንና እስከ ሚያዝያ ወር በነበረው ጊዜ በአብዛኛው የምስራቅ አፍሪቃ የአርብቶ አደሮች አከባቢዎች የግጥሽ መሬቶች በመድረቃቸው በኢትዮጵያ 400,000 የሚሆኑ ተጨማሪ ሰዎች ረድኤት እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት አገልግሎት ቃል አቀባይ አቶ አክሎግ ንጋቱ “በአሁኑ ወቅት ለሶስተኛው ዙር በአንድ ሶስተኛ ያነሰ ገንቢ ምግብ እያከፋፈልን ነው። የበቆሎና የአኩሪ አተር ድብልቅ የሆነ የገንቢ ምግብ እጥረት ስላለብን ልናቀርበው አልቻልንም። ይህን ውሱን ምግብ ለማግኘት ሸሪኮቻችንን እየጠይቀን ነው።” በማለት ስለሁኔታው አስረድተዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG