በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኢትዮጵያና ኤድስ ዛሬ

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ሥርጭትና የኤድስ ሞት መጠን መቀነሱ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መቆጣጠሪያ ፕሮግራም ዩኤንኤድስ ጋር በመተባበር ያወጣው የቅኝት ሪፖርት በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ሥርጭት በ20 ከመቶ፤ ኤድስ የሚያስከትለው ሞትም እንዲሁ በ20 ከመቶ መቀነሱ ዓለምአቀፍ የኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በወጣ ሪፖርት ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያ በሌሎችም የወረርሽኙ ቁጥጥር ዘርፎች የወሰደችውን እርምጃ እንዲያስረዱ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራን ትዝታ በላቸው አነጋግራለች።

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ሀፍቶምና የልቦናው ብርሃን

Haftom Kahsay

ሀፍቶም ካህሣይ የቪኦኤ "ሕይወት በቀበሌ" እንግዳ ነው፡፡

ሀፍቶም ካህሳይ በመቀሌ ሐይደር ቀበሌ ውስጥ ይኖራል። ገና የአሥራ አንድ ዓመት ልጅ እያለ ነው በደረሰበት ችግር ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣው። አሁን ሃያ ሦስት ዓመት የሞላው ሲሆን፥ በዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርቱን እየተከታተለ በትርፍ ጊዜ ይሠራል። ማየት ለተሳናቸው የሚጠቅሙ መጻሕፍትም በድምፅ ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ነው።

የዚህን ወጣት ታሪክ በ"ሕይወት በቀበሌ" ዝግጅት ቀርቧል።

ሀፍቶም መቼና እንዴት የዓይን ብርሃኑን እንዳጣ፤ የሕይወቱን ጎዳናና የወደፊት ራዕዩን ይናገራል፡፡

ለዝርዝሩ የግርማይ ገብሩን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG