በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኢትዮጵያ ፓርላማ የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን አፀደቀ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚያገለግለውን የእድገትና የመሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ አፀደቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎች ለዕቅዱ ስኬት አብረው እንዲሰለፉ ጥሪ አቀረቡ።

ብቸኛው የመድረክ ተወካይ ግን ዕቅዱ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምኃን ዘገባ ያዳምጡ።

የዓለም ኤድስ ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲታሰብ

የዘንድሮውን የዓለም ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎች ለተለያዩ ጫናዎች ሳይበገሩ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁና ከግባቸው እንዲደርሱ ያሳሰቡ ስብሰባዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ቅጥር ግቢዎች ተካሂደዋል፡፡ ተማሪዎቹም በዝግጅቶቹ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በተካሄዱት በእነዚህ ስብሰባዎች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከፍ ወዳሉ ደረጃዎች የደረሱ ሰዎች የሕይወታቸውን ተሞክሮ ለተማሪዎች ተርከዋል፡፡ ተማሪዎቹም ንግግር ላደረጉ እንግዶች የመሰሏቸውን ጥያቄዎች በማንሣት ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፤ ያገኙትን ትምህርትና ዕውቀትም መልሰው አንፀባርቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካልቲ ተገኝተው ለተማሪዎቹ የሕይወት ተሞክሯቸውን የሰጡት የአቢሲኒያ ፍላይት ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካፕቴን ሰሎሞን ግዛው እና የዘመን ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ብሩታዊክ ዳዊት አብዲ ነበሩ፡፡

ሁለቱም ተናጋሪዎች በሕይወት ውጤታማ ለመሆን ማንም ራዕይ እንደሚያስፈልገው፣ በዚህም ላይ በብርታት መሥራት፣ በጥንቃቄ መኖር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG