በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ስለደርግ ባለሥልጣናት የዕርቅና የይቅርታ ጥያቄ ቀረበ፡፡

በደርግ ዘመን የተፈፀሙ በደሎችንና ጥፋቶችን ሃገራዊ ይቅርታና ዕርቀሠላም ባሉት መንገድ ለመጨረስ አራት የኢትዮጵያ አብያተ-ዕምነት መሪዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጥሪ አቀረቡ፡፡

በያዝነው ታኅሣስ መጨረሻ የሠላምና የዕርቅ በዐል ለማድረግም ዕቅድ ተይዟል፡፡

የኃይማኖት መሪዎቹ ዕሁድ ታኅሣስ 10 ቀን 2003 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፁት የይቅርታና ዕርቁ ጥረት የተጀመረው ከሁለት ዓመታት ወዲህ ነው፡፡

ለዚህም ጥረት መነሻ የሆነው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በፍርድ ሥር የሚገኙ የደርግ ባለሥልጣናትና በተለያዩ ደረጃዎች ይሠሩ የነበሩ ታራሚዎች ባቀረቡላቸው ጥያቄ መሠረት እንደሆነም የኃይማኖት መሪዎቹ የፅሁፍ መግለጫ ያረጋግጣል፡፡

የኃይማኖት መሪዎቹን ወክለው ጥሪውን ያሰሙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ አባ ጳውሎስ ናቸው፡፡

አቡነ ጳውሎስ በዚሁ ጥሪ "... ልጆቻችን ቂም በቀልን መውረስን አስወግደው በሠላም፣ በፍቅርና በመቻቻል እንዲኖሩ፣ ወደፊትም ተመሣሣይ አስከፊ ድርጊት በኢትዮጵያ ታሪክ ፈፅሞ እንዳይደገም የዕርቅና የይቅርታ መልዕክታችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት በመተማመን ደፍረን እናቀርባለን፡፡" ብለዋል፡፡

ጥሪውን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ የሱስ ናቸው፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ባክነር/ብራይት ሆፕ ት/ቤት (ባንቱ/ኢትዮጵያ)

"ድኃይቱ ሃገር በበረከተ የውጭ ወረት እየነቀዘ ባለው ማኅበራዊ መዋቅር ላይ ዐይኗን ስታሣርፍ"

ኢትዮጵያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ተቀባይነት ካለው ሥነ-ምግባር ተፃራሪ በሆነ ሁኔታ የሚንቀሣቀሱ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ማሣደጊያዎችን ለመዝጋት እያቀደች መሆኑን የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን ፒተር ሃይንላይን ያስተላለፈው ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል ቀደም ሲል መተላለፉ ይታወሣል፡፡

ያንን በማጭበርበርና በውንብድና አድራጎት ታጭቋል የተባለ፤ እንዲያውም ሥር ሰድዶ መንሠራፋቱና በገንዘብ ጥቅምም መተሣሰሩ የሚነገርለትን አሠራር ለማፅዳት ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሊያስፈልግ እንደሚችል ፒተር በዘገባው ሁለተኛ ክፍል ጠቅሷል፡፡

"የአዲስ አበባውን ቦሌ ዓለምአቀፍ የአየር መናኸሪያ" ከመዋዕለ-ሕፃናት ጋር ለማምታታት የሚዳዳበት ጊዜ ጥቂት አይደለም" ብሎ ነው ፒተር የዘገባውን ሁለተኛ ክፍል የሚጀምረው፡፡ ግማሽ ለሚሆኑት መድረሻቸው ዩናይትድ ስቴትስ የሆነ በየቀኑ በአማካይ 12 ኢትዮጵያዊያን ሕፃናት በአዳዲሶቹ የውጭ አሣዳጊዎቻቸው እቅፍ ውስጥ እየሆኑ በዚህ በኩል ያልፋሉ፡፡

ከሰባት ዓመታት በፊት የባሕር ዘለሎቹ የጉዲፈቻ ልጆች ኢትዮጵያዊ የሚገኘው ከሁለት መቶ አንድ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ግን ከአምስቱ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሕፃን ነበር፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG