በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዩናይትድ ስቴትስ ለታዳጊ ሀገሮች ቤተሰቦች ጤናና የአካባቢ ደህንነት ጠንቅ የሆኑ ምድጃዎችን ለማስወገድ እገዛ ልታደርግ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በቤቶች ውስጥ በምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ጢስ ምክንያት የሚደርሱ ችግሮችን ለማስወገድ የንፁህ ምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ዓለምአቀፍ ጥምረት (Global Alliance for Clean Cook Stoves) የተባለና በቤተሰብ ጤና ላይ ጠንቅ የማይፈጥሩ የምግብ ማብሰያዎችን ለማስተዋወቅና ለማዳረስ የታቀደ ዓለም አቀፍ ህብረት ማደረጃ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር ልትሰጥ ቃል መግባቷን ባለፈው ሰሞን በዚሁ በሴቶችና ቤተሰብ ፕሮግራም ማቅረባችን ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ነበሩ ይህን ይፋ ያደረጉት።

እንደአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር እስከ ሁለት ሺህ ሃያ ባለው ጊዜ ውስጥ መቶ ሚሊዮን የታዳጊ ሀገሮች ቤተሰቦችን የጤናም ሆነ የኣካባቢ ደህንነት ጠንቅ ከሆኑ ማብሰያዎች ለማላቀቅና የተሻሉ ምድጃዎችን ለማዳረስ የታለመ ዕቅድ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ማብሰያ ይዞታ ምን ይመስላል? ለመሆኑ በሀገሪቱ የፀሐይ ችግር እንዳለመኖሩ የፀሐይን ኃይል ለመጠቀምና ለማስለመድስ ምን ያህል ጥረት ይደረጋል?

ወጣት በረከት ደሴ ሶላር በረከት የተባለ ድርጅት መሥራች ሲሆን በፀሐይ ኃይል ምግብን ማብሰልን እና ሌሎችንም የተሻሉ ምድጃዎችን ድርጅቱ ያመርታል። ስላሉት አማራጭ ምድጃዎች ያወሣል፡፡ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩትን በብዛት ማስለመድ አስፈላጊነቱን አጥብቆ ያምንበታል። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ቢቢሲ ጌልዶፍን ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት እኔም ልጠየቅ ይገባል አለ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በዜና ሥርጭቱ "የኔም ስም ነው የጎደፈው" በማለት ቢቢሲ ይቅርታ እንዲጠይቅ መግለጫ አውጥቷል።

ቢቢሲ ዘገባውን ባሠራጨበት ጊዜ "የዘገባውን ትክክለኛነት አውቃለሁ" ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ቃለ ምልስስ የሰጡትን "በወቅቱ የህወሓት ታጋይ የነበርኩ" የሚሉትን አቶ ገብረመድኅን አርአያን አነጋግረናል፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG