በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

"በደኃው ኢትዮጵያዊ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች መረገጥ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትና የለጋሽ አገሮች ቡድን አቋም የተቀራረበ ነው" ሲል የተቃዋሚዎች ጥምረት፣ መድረክ ከሰሰ።

ዓለም አቀፍ የስብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከለጋሾች የሚሰጠውን እርዳታ ለፖለቲካ መጨቆኛ ያውለዋል ሲል ያወጣውን ዝርዝር ሪፖርት የለጋሽ አገሮች ስብስብ የሆነው ዳግ (DAG) መቃወሙ ይታወሳል።

መድረክ ይህን እርምጃ ተቃውሞ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከቁብ ያለመቆጠሩ አሳዝኖናል ብሏል ።

ዳግ፥ እርዳታ ለፖለቲካ መሣሪያነት እየዋለ ነው የሚለውን ስሞታ ተከትለን ባደረግነው ማጣራት እንደዚያ ያለ ሁኔታ አለመኖሩን አረጋገጠናል የሚል አስተያየት መሠንዘሩን የመድረክ መግለጫ ጠቅሶ የማጣራቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ስምምነት የተደረሰባቸውን የቁጥጥር ዘዴዎች ብቃትና ጥንካሬ በመመዘን የተገደበ የቢሮ ሥራ እንጂ የተባሉትን ክሦች የማጣራት ዓላማ አልነበረውም ብሏል። "ለዴሞክራሲና ለስብአዊ መብቶች ትልቅ ክብር እንሰጣለን" የሚሉት ለጋሽ አገሮች ቅድሚያ ሊሰጡት ይገባ የነበረው ይህ የመብቶች "የዳግ ሪፓርት ዋና ጭንቀት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመፈጸሙ ምክንያት እርዳታው እንዳይቋረጥ በሚል ሽፋን ነገሮችን ተሽቀዳድሞ ማድበስበስ ነው" ብሏል መድረክ በመግለጫዉ። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

የምርጫው ውጤትና የኦባማ አስተዳደር ዕቅዶች፤ የምርጫ ውጤት አቀባበልና ዲሞክራሲ።

በትላንቱ የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ፥ ሪፐብሊካኖች ያገኙት ከፍተኛ ውጤት ከዲሞክራት ፓርቲ ወገን ለሆኑት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ቀጣይ ሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመን አጀንዳዎች ዳር መድረስ ይበልጥ አዳጋች ሁኔታዎችን መደቀኑ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

የምርጫው ውጤትና ቀጣዩ ሂደት የሚተነትኑልን ዶ/ር መሠረት ቸኮል በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በዊስከንሰን ዩኒቨርሲቲ ሪቨሪቨር ፎልስ የጋዜጠኝነትና የኮምዩኒኬሽን መምህር ናቸው።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG