በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኢትዮጵያዊያን በየመን በችግር ላይ

ኢትዮጵያዊያን ሥራ ፈላጊ ተዘዋዋሪዎች በየመን ከተማ ሃራዳ በችግር ላይ ይገኛሉ።

ቁጥራቸው ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጋ ሥራ ፈላጊ ተዘዋዋሪ ኢትዮጵያዊያን ሃራዳ በተባለች ሰሜናዊት የየመን ከተማ ያለ ምግብ፣ ውኃና መጠለያ መሄጃ አጥተው ይገኛሉ።

ሃራዳ ውስጥ መውጫ አጥተው ከሚገኙት መካከል ከሳሊም አህመድ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገናል።

ሳሊም ሰይድ ከሁለት ወራት በፊት ከጂዳ ተባርረው ወደ ሃራዳ እንደተወሰዱ ገልፀውልናል። በሃራዳ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉና ገሚሶቹ እንደርሳቸው ከጂዳ ከጂዛንና ከሪያድ ተባርረው የመጡ እንደሆኑ፥ የተቀሩት ግን በህገ ወጥ መንገድ አሾልከው ድንበር ለሚያሻግሩ እየከፈሉ ከኢትዮጵያ በሶማሊያና በጂቡቲ ድንበር አቋርጠው፣ በጀልባ በአደን ባህረ ሰላጤ ከዚያም በእግር የመን የገቡ ናቸው ብለዋል።

ሰዎቹ ሥራ ፈላጊዎች እንጂ የፖለቲካ ስደተኞች አይደሉም ያሉት አቶ ሳሊም አብዛኞቹ ወጣቶች እንደሆኑና ሴቶችም እንደሚገኙባቸው ገልፀውልናል። መጠለያ ስለሌላቸው ሜዳ ላይ ተበትነን እንገኛለን። ቀይ መስቀል በቀን አንዴ ከሚሰጠን ደረቅ ሩፒና ዳቦ በስተቀር ምግብ ወይም ህክምና የለንም ነው ያሉት አቶ ሳልም፡፡ እንዲያም ሆኖ በባዕድ አገር ሠርቶ መብላት ለለመዱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር መመለስ ከባድ እንደሚሆን አልሸሸጉም፡፡

ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ።

የዞንጊ ደን

ወርዒ ለኸ

በትግራይ ዞንጊ ቀበሌ ከበረሃነት ወደ ደንነት ተለውጣለች፡፡

በትግራይ ክልል የአድዋ ሠንሠለታማ ተራሮች በመባል የሚታወቁት ከፍተኛ ቦታዎች በታሪክ በጥሩ መልኩ ቢታወሱም የተራቆቱ ስለመሆናቸው ግን እውነት ነው፡፡ በጦርነትና በድርቅ አደጋ ምክንያት አካባቢው የነበረውን የደን ሽፋን እያጣ መምጣቱ በግልፅ ይታያል፡፡

ይህም ሆኖ ግን የተራቆተውን መሬት እያዩ ብቻ ከማዘን ይልቅ በጥሩ ምሣሌነት የሚጠቀስ አካባቢ መመልከት ተመራጭነት ይኖረዋል፡፡

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን የወርዕይ ወንዝን ያካለለው ሥፍራ ወርዒ ለኸ የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡

ከመቐለ በሓውዘን በኩል የነበለትን ከተማ በማለፍ ዕዳጋ ዓርቢ የሚባለው የወረዳው ማዕከል የሆነው ከተማ እስኪገባ ድረስ የአካባቢው የደን ሽፋን ገና በማቆጥቆጥ ላይ ይገኛል፡፡

የዕዳጋ ዓርቢን ከተማ አልፈው ወደ አድዋ በሚወስደው በረሃማ የገጠር መንደር ዞንጊ የሚባል ቦታ ግን በሚገርም ሁኔታ በደን ተሸፍኗል፡፡ በሃገር በቀል ደን የተሸፈነው ይህ ሥፍራ ከሌላው አካባቢ በተለየ ሁኔታ ነፋሻ ደሴት ሆኖ ይታያል፡፡ በአካባቢው ያለው ሙቀት በዚህች ቀበሌ ነፋሻ አየር ውስጥ ተውጦ ይቀራል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ይመልከቱ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG