በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

USA Votes 2010

ማክሰኞ ጥቅምት 23, በ50ውም የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች መራጮች ግዛቶቹን የሚያስተዳድሩ ገዢዎች ይመርጣሉ። የአካባቢ ጉዳዮቻቸውን በብሄራዊው ምክር ቤት መድረክ ትኩረት እንዲያገኝ ለሚያደርጉላቸው ፖለቲከኞችም ድምፃቸውን ይሰጣሉ።

የአገሪቱ ልብ ትርታ በነገው የብሄራዊ ሸንጎ ሸንጎ፥ «የትኛው አሸናፊ ይሆናል?» የሚለውን የተከተለ ነው። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ምርጫ የሚመለከታቸው መላው የህግ አውጭው ምክር ቤት አባላትና በየ6 ዓመቱ ከሚመረጡት የህግ መወሰኛው ምክር አባላት አንድ ሦሥተኛው በቀጣዩ ምክር ቤቶች የሚኖራቸው ሚና ማክሰኞ ይወሰናል። ውጤቱም የግለሰብ ዕጩዎቹን ብቻ ሳይሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት፥ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2008 በተካሄደው ከፍተኛ ድምፅ በተመረጡት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራቲክ ፓርቲና በተቀናቃኙ የሪፐሊካን ፓርቲ መካከል የቀጣዩን የፕሬዝዳንቱን አጀንዳዎች ስኬት ጭምር ይወስናል።

በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ማክሰኞ ጥቅምት 23 የሚካሄዱት Midterm Elections በመባል የሚታወቁት የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት አብላጫውን የሁለቱን ምክር ቤቶች የኅግ አውጪውንና የእንደራሴዎች ምክር ቤቶች፤ መቀመጫዎች ለያዘው የፕሬዝዳንት ኦባማ የዲሞክራቶች ፓርቲ ፈተና ይደቅናል፤ ተብሎ ተገምቷል።

የሪፐብሊካኑ ፓርቲ የብልጫውን ድምፅ ያገኝ ይሆናል፤ የሚል ሠፊ ግምት በተያዘባቸው በእነኚህ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በርካታ መቀመጫዎችን ያጡ ይሆናል የተባሉት ዲሞክራቶች፥ ከተቀናቃኛቸው በሚገጥማቸው ፈተና፥ ከዲሞክራቱ ፓርቲ የሆኑት ፕሬዝዳንት ኦባማ በቀጣዩ የሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ለማሳካት ያቀዷቸው ውጥኖች «ይደናቀፋሉ፤» የሚል ግምት አሳድሯል።

እንደ ቅድመ ምርጫ ትንበያዎቹ ሪፐብሊካን የሁለቱንም ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎች ከያዙ፥ የተባሉት ለውጦች፥ በአገር ውስጥ ጉዳዮች ብቻ ሳይወሰኑ፥ የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ ጨምሮ፥ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምታጨወታቸው «ዋና ዋና የሚሰኙ ሚናዎቿም ይንፀባረቃሉ፤» እየተባለ ነው።

በርዕሱ ዙሪያ ትንታኔ የሚሰጡን የፖለቲካ ሳይንቲስት ጋብዘናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያ ናቸው።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG