በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ማክሰኞ ጥቅምት 23 የሚካሄዱት Midterm Elections በመባል የሚታወቁት የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት አብላጫውን የሁለቱን ምክር ቤቶች የኅግ አውጪውንና የእንደራሴዎች ምክር ቤቶች፤ መቀመጫዎች ለያዘው የፕሬዝዳንት ኦባማ የዲሞክራቶች ፓርቲ ፈተና ይደቅናል፤ ተብሎ ተገምቷል።

የሪፐብሊካኑ ፓርቲ የብልጫውን ድምፅ ያገኝ ይሆናል፤ የሚል ሠፊ ግምት በተያዘባቸው በእነኚህ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በርካታ መቀመጫዎችን ያጡ ይሆናል የተባሉት ዲሞክራቶች፥ ከተቀናቃኛቸው በሚገጥማቸው ፈተና፥ ከዲሞክራቱ ፓርቲ የሆኑት ፕሬዝዳንት ኦባማ በቀጣዩ የሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ለማሳካት ያቀዷቸው ውጥኖች «ይደናቀፋሉ፤» የሚል ግምት አሳድሯል።

እንደ ቅድመ ምርጫ ትንበያዎቹ ሪፐብሊካን የሁለቱንም ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎች ከያዙ፥ የተባሉት ለውጦች፥ በአገር ውስጥ ጉዳዮች ብቻ ሳይወሰኑ፥ የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ ጨምሮ፥ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምታጨወታቸው «ዋና ዋና የሚሰኙ ሚናዎቿም ይንፀባረቃሉ፤» እየተባለ ነው።

በርዕሱ ዙሪያ ትንታኔ የሚሰጡን የፖለቲካ ሳይንቲስት ጋብዘናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትን ለመቆጣጠር በዕጩ እንደራሴዎች መካከል የሚካሄደው የምረጡኝ ዘመቻ ተጠናክሮ ሰንብቷል።

የሁለቱም ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪ ዕጩዎችም እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ እየታገሉ ይገኛሉ።

በሕዝብ አስተያየቶችና በፖለቲካ ሙያተኞች ግምት በዘድሮው 2010 የአማካይ ዘመን ምርጫ ወይም ሚድ ተርም ኤሌክሽን የመጨረሻ ቀናት ውድድር ሬፐብሊካን ተፎካካሪዎች በብዙው ሣይቀናቸው እንደማይቀር ይወራል። የዚህ ምክንያት ደግሞ ከአገሪቱ ወቅታዊ የኤኮኖሚ ሁኔታ ጋር ይያያዛል።

ለመሆኑ ሚድ-ተርም ወይም የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ምን ማለት ነው? ሁኔታውን እንደ ኢትዮጵያ ካሉ አገሮች ጋር ማያያዝስ ይቻል ይሆን? ባለሙያ አነጋግረናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ-ማርያም ይባላሉ። የህግ ጠበቃና በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ናቸው። ያወያያቸው ያዲሷበበ መነሻ ጥያቄም ይኸው ነው። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG