በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን አደገኛ ሁኔታ ላይ ናቸው

ደቡብ ሱዳን፤ ስቴቶቿና ጎረቤቶቿ
ደቡብ ሱዳን፤ ስቴቶቿና ጎረቤቶቿ

ደቡብ ሱዳን፤ ማላካል ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከበደና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በግጭት ተፈናቅለው ከሚገኙ የውጭ ዜጎች ጥቂቱ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በግጭት ተፈናቅለው ከሚገኙ የውጭ ዜጎች ጥቂቱ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ደቡብ ሱዳን፤ ማላካል ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከበደና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙት ከሃገሪቱ ነፃ መውጣት ጋር ተያይዞ የአካባቢው ሃገሮች ዜጎቻቸው ያለድንበር፣ ጉምሩክና ሌላም ቁጥጥር እየገቡ የአዲሲቱን ሃገር ምጣኔ ኃብት እንዲያጎብቱ ለማገዝ አስበው በወሰዱት እርምጃ እንደነበር ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልፀዋል፡፡

በተለይ ሰሞኑን የአፐር ናይል ግዛት ዋና ከተማ ማላካል በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር ከወደቀች ወዲህ ኢትዮጵያዊያኑ ብዙ በደልና እንግልት እንደደረሰባቸው፤ በሴቶችም በወንዶችም ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም፣ እስከ ሐሙስ፣ ታኅሣስ 17 / 2006 ዓ.ም ባለው ጊዜም ቢያንስ የሰላሣ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት መጥፋቱን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር /ፎቶ ፋይል/
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁባ እንደነበሩ መስማታቸውን፤ እንዲሁም ጁባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደውለው ያሉበትን ሁኔታ መናገራቸውንና ምንም የመፍትሔ ምላሽ አለማግኘታቸውን እነዚሁ በጭንቀት ላይ ነን የሚሉ የአፐር ናይል ስቴት ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ
ደቡብ ሱዳን ና ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንግሥትም እንዲደርስላቸውና ከዚያ በአፋጣኝ እንዲያወጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG