ረሃብ በአፍሪካ - የአሜሪካ ድምፅ
ረሃብ በአፍሪካ - የአሜሪካ ድምፅ
የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ
            <description>በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
በስምምነቱ መሰረትም የርዳታ እህሉ እየገባ መኾኑን አንድ የኃይማኖት አባት ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመኾኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብለዋል።
የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም ከ110 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ16 ሺሕ ኩንታል በላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መኾኑን አስታውቀዋል።
የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር...</description>
“ሱዳን ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” - ዓለም አቀፍ ነፍስ አድን ኮሚቴ
            <description>በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” ሲል የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ አመለከተ፡፡
በተቃናቃኞቹ ጀኔራሎች መካከል በቀጠለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 12 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተቋሙ ዘገባ ጠቅሷል፡፡
ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉት በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶች በወደሙባቸው አካባቢዎች የሠፈሩ ሲሆን የጅምላ ረሃብ ሥጋትም ተጋርጦባቸዋል።
ዓለም አቀፉ ድርጅት በሱዳን ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ መጋለጡን ገልጾ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ ገጥሟታል ብሏል፡፡
“ከዓለም ሕዝብ ከአንድ ከመቶ ያነሰ የሕዝብ ብዛት...</description>
በጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ ምክኒያት ረሃብ እየተስፋፍ መኾኑን ተመድ አስታወቀ
            <description>ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ አኹንም በመላው ዓለም እየተስፋፋ ላለው ረሃብ ምክኒያት መኾናቸውን በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት።
አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በተጠናቀቀው ዓለምን ከረሃብ  ነጻ የማድረግ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት፣የድርጅቱ ዋና ሓላፊ ጌራልድ ሙሌር፣  ረሃብ የዓለምን ሕዝብ እየጎዳ ያለው የበለፅጉት ሃገራት ከዓመት ገቢያቸዉ በየዓመቱ ለአዳጊ ሀገራት ሊያደርጉ የሚገባቸዉን ድጋፍ ባለመስጠታቸውና በአዳጊ ሀገራትም የፖለቲካ ውሳኔ  ባለመኖሩ መኾኑን ገልፀዋል። የአፍሪካ ኅብረት በበኩሉ ከአራቱ አንዱ አፍሪቃው ለረሃብ ችግር የተጋለጠ መሆኑን ገልፆ፣ ግጭት አሁንም ለረሃብ መስፋፋት ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የርዳታ በሮች ለተዘጉበትና ለተራበው የሱዳን ሕዝብ ሾርባ የሚመግቡ የማኅበረሰብ አባላት
            <description>በጦርነት በታመሰችው ሱዳን ኡምዱርማ ውስጥ የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከግል ለጋሾች ባገኙት ጥቂት ድጋፍ  ሾርባ እየሠሩ የተራቡትን በመመገብ ላይ ናቸው።
ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቅርቡ ባወጡት መግለጫ፣ “በሱዳን የሚገኙ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ለጋሽ ድርጅቶች የርዳታ እህል እዳያስገቡ በተቀነባበረ ሁኔታ ክልከላ ያደረጉ ነው ባሉበት በአኹኑ ሰዓት ከለጋሽ ድርጅቶች ገደብ የሌለው ማለፊያ እንዲሰጡ እየወተወቱ ባለበት በዚህ ወቅት አንዱ የሱዳን ክፍል በከፍተኛ ርሃብ ተጠቅቷል” ሲል የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ሄነሪ ዊልከንስ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ በከባድ ድሕነት ውስጥ እንደሚኖር ትላንት ሐሙስ የወጣ ሪፖርት አመለከተ
            <description>የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እና የብሪታኒያው ኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ያወጡት ሪፖርት ሲሆን ከመካከላቸው ከግማሽ የሚበልጡት ሕጻናት መሆናቸውን አስታውቋል።
አርባ ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በጦርነት በሚታመሱ እና በአስተዳደር እና በምጣኔ ሀብት ደካማ በሆኑ ሀገሮች መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም እና የኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲው የድህነት እና የሰብዓዊ ዕድገት መርሐ ግብር ያወጡት የዘንድሮው ሪፖርት በጠቅላላው ስድስት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ሕዝብ የሚኖርባቸው 112 ሀገሮችን መረጃ ያካተተ ነው።
በሪፖርቱ ሰንጠረዥ መሠረት በከፋ ድሕነት ከሚኖሩት 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሰዎች ውስጥ ግማሽ ገደማ የሚሆኑት የሚኖሩት በአምስት ሀገሮች እንደሆነ ተጠቁሟል። ህንድ 234 ሚሊዮን፥ ፓኪስታን 93 ሚሊዮን፥ ኢትዮጵያ 86 ሚሊዮን፥ ናይጄሪያ 74...</description>
‘የአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ዋስትና እጦት በአፍሪካ በፍጥነት እያደገ ለመጣው የሕዝብ ቁጥር ስጋት ጋርጧል’ - ባለሞያዎች
            <description>የአየር ንብረት ለውጥ እና የዓለም ሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት መጨመር የምግብ ዋስትናን አደጋ ላይ ሊጥል የመቻሉ ዕጣ እያነጋገረ ነው። እንደ ባለሞያዎችም እምነት የዓለም ህዝብ ቁጥር ከ10 ቢሊዮን በላይ ሲደርስ የሰብል ምርት በአንጻሩ በ30 በመቶ ሊቀንስ ይችላል።
መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ የመንግሥታቱን ድርጅት የዓለም ሕዝብ ቀን አስታኮ ባጠናቀረው ዘገባ እንደጠቆመው፤ ሁኔታው በተለይ በአፍሪካ የሚኖረውን ተጽዕኖ ለመቀነስ፤ በግብርናው ዘርፍ የሚደረግ ለውጥ ብቸኛው አማራጭ ነው።
ለዝርዝሩ አሉላ ከበደ።
በሱዳን ከ756 ሺሕ በላይ ሕዝብ የከፋ የምግብ እጥረት ሊገጥመው እንደሚችል ተሰግቷል
            <description>በሱዳን የተከሰተው ረሃብ ከቸነፈር ደረጃ ላይ መድረስ ያለመድረሱን ለመወሰን የመንግሥታቱ ድርጅቶች የተለያዩ ተቋማት እና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ባቀረቡት የቅድመ ትንበያ ውጤት መሰረት፣ ከ756 ሺሕ ሕዝብ በላይ ለከፋ የምግብ እጥረት ሊጋለጥ  እንደሚችል ተሰግቷል።
የመጀመሪያው የትንበያ አሃዞች፤  እስካለፈው ግንቦት 24, 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ በጦርነት በተበታተነችው አገር ውስጥ የታየውን 'በፍጥነት እያሽቆለቆለ ያለ ሁኔታ የሚያመላክቱ ናቸው’ ተብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በሰጡት አስተያት፣ በዓለም ግዙፍ የሰብአዊ ቀውስ በተከሰተበት የሱዳን ምስቅልቅል 12 ሚሊዮን ሕዝብ ከቀዬው መፈናቀሉን ተናግረዋል። 
"በአንዳንድ ግዛቶች እጅግ መጠነ ሠፊ የረሃብ አደጋ በተንሰራፋበት ባሁኑ ወቅት ነዋሪዎች...</description>
በሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከረኀብ ጉዳት ጋራ በተያያዘ አንድ ሰው መሞቱ ተገለጸ
            <description>በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰሃላ ሰየምት ወረዳ፣ ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች ለኅልፈት መዳረጋቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በወረዳው ያጋጠመውን ድርቅ ተከትሎ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ24ሺሕ በላይ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፤ ባለፈው ሚያዝያ ወር፣ ከረኀብ ጉዳት የተነሣ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን፣ ከጤና ተቋማት ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል፡፡
በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የቢላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ በበኩላቸው፣ በቢላዛ ቀበሌ ብቻ ባለፈው ወር ሁለት ሰዎች ከረኀብ ጉዳት ምክንያት መሞታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የርዳታ መቆራረጥ፣ የጸጥታ እና የመንገድ አለመኖር ችግሩን እንዳባባሰውም...</description>
"በሱዳን የተደቀነው የረሃብ ቸነፈር አደጋ እየተባባሰ ነው" የዓለም የምግብ ፕሮግራም
            <description>በጦርነት በተጎዱት የሱዳን አካባቢዎች ቁጥሩ ወደ አምስት ሚሊዮን በሚጠጋ ህዝብ ላይ የተደቀነው የረሃብ ቸነፈር አደጋ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ ነው ሲል የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስጠነቀቀ። በዚህ ሳምንት ሱዳንን ጎብኝተው የተመለሱት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ካርል ስካዉ ትናንት ረቡዕ ባወጡት መግለጫ የረሃቡ ሁኔታ በፍጥነት እያሽቆለቆለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የከበደ ቸነፈር አፋፍ ላይ ለሚገኘው ህዝብ የሰብዓዊ ረድዔት ተደራሽነትን እናመቻቻለን ብለው ቃል የገቡት ወገኖች በሙሉ አሁኑኑ በተግባር ሊተረጉሙት  ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ዳርፉር እና ኮርዶፋን አካባቢ የክረምቱ ዝናብ ወቅት ገብቶ መንገዶች ከመዘጋጋታቸው በፊት የምግብ አቅርቦት ለማከማቸት ያለው የጥቂት ሳምንታት ጊዜ ብቻ መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለስልጣኑ መግለጫ...</description>
ተመድ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ ርዳታ የሚውል 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ አቅዷል
            <description>የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ለምትታመሰው፣ በጎርፍ እና ድርቅ ለተጠቃችው ኢትዮጵያ የሚያስፈልገውን የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት ከፍ ለማድረግ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ማቀዱን ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ።
ከኢትዮጵያ እና ከእንግሊዝ መንግሥታት ጋራ በመተባበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጄኔቫ ላይ ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለ15.5 ሚሊዮን ሰዎች የሚሆን የነብስ አድን ርዳታ እና ለተጨማሪ 10 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች የሚሰጠውን የምግብ ዕርዳታ መጠን ለማሳደግ የታለመ መሆኑ ተመልክቷል።
“የአስቸኳይ ርዳታ የሚጠይቁት ሁኔታዎች በድርቅ እና በጎርፍ እንዲሁም በግጭት እየተባባሱ የመጡ ናቸው” ሲል ተመድ አስታውቋል።
"ኤልኒኞ በሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል በሚገኙ ደጋማ አካባቢዎች ያለውን ድርቅ በማባባሱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የውሃ አቅርቦት ዕጥረት፤ የግጦሽ...</description>
ድርቅ የብሄራዊ አደጋ ሥጋት የደቀነባት ማላዊ የርዳታ ጥሪ አሰማች
            <description>በተፈጥሮ የሚከሰተው ኤልኒኞ፣ በፓስፊክ ምሥራቃዊ ውቅያኖስ አካባቢ ከሚታየው ያልተለመደ የውሃ ግለት የሚነሳው ሙቅ አየር በዓለም ዙሪያ የአማካይ ሙቀት መጠን እንዲጨምር በማድረጉ እና እንዲሁም ወደ ከባቢ ዓየር የሚለቀቀው በካይ የካርቦን መጠን የከሰቷቸው ሁኔታዎች ተደራርበው ድፍን ደቡባዊ አፍሪቃ ባለፉት ዓመታት አጋጥሞት በማያውቅ አስከፊ ድርቅ እየተናጠ ይገኛል። ይህንንም ተከትሎ ማላዊ፣ ዝምባብዌ እና ዛምቢያ ባለፈው ወር አከባቢውን በመታው ድርቅ ሳቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል።
የምግብ አቅርቦት ምንጮች እየነጠፉ ባሉባት ማላዊ፡ የማሳ ሰብል ስርቆት ብርቱ ችግር እየሆነ ነው። የበቆሎ አምራች የነበሩ ኡላሊያ ላፑሶኒ የተባሉ አንዲት ገበሬ ሲናገሩ፡ በድርቁ ሳቢያ የዘሩት በቆሎ ባለማፍራቱ በአሁኑ ወቅት የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
"እስኪ አስቡት ለዚህ ወር የሚሆን ምግብ...</description>
ተመድ በኢትዮጵያ ለተረጂዎች ርዳታ ለማቅረብ የ998 ሚሊየን በጀት ክፍተት እንዳለበት አስታወቀ
            <description>የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ መስከረም ወር ባለው ጊዜ አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ከሚገመቱ ዘጠኝ ሚሊየን ተረጂዎች ውስጥ አምስት ሚሊየን ለሚሆኑት ብቻ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን እና ለቀሪዎቹ አራት ሚሊየን ተረጂዎች ተጨማሪ 998 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጠሉ ግጭቶች እና ድርቅን እና ጎርፍን ጨምሮ የአየር ንብረት አደጋዎች አሉታዊ ተፅእኖ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ዋስትና እጦት እንዲባባስ በማድረጋቸው፣ እ.አ.አ በ2024 ከመጋቢት እስከ መስከረም ባለው ወር 9 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በትላንቱ መግለጫው አስታውቋል።
ከነዚህ ውስጥ በተጠቀሰው ጊዜ...</description>
የመንግስታቱ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ17 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ መደበ
            <description>በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለመጣው የምግብ ዋስትና እጦት የ17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ አስታወቁ። አዲስ የተመደበው ይህ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ለተጨማሪ አደጋ ያጋለጠው ‘ኤልኒኞ’ የአየር መዛባት ያስከተለው ድርቅ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የከፋ ጉዳት ሊያስከትል መቻሉ ያሳደረውን ብርቱ ስጋት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያን የገጠመው የምግብ ዋስትና እጦት በመጭው ወራትም እየበረታ ሊሄድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ከሐምሌ እስከ መስከረም ባሉት የክረምት ወራት ውስጥ በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከዚህ ቀደም የተከሰተው ድርቅ እና በሃገሪቱ ያሉት ግጭቶች አሁንም ተጽዕኖ ማሳደራቸውን...</description>
በኢትዮጵያ እያሻቀበ ላለው የተረጂዎች ቁጥር ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ
            <description>በኢትዮጵያ ለተረጂዎች የምግብ ርዳታ ለማቅረብ 3ነጥብ4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቁ። የተረጅዎች ብዛት በተያዘው ዓመት 10ነጥብ4 ይደርሳል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ አታለለ አቡሃይ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የተረጅዎች ብዛት 6ነጥብ6 ሚሊዮን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በጎርፍ እና በሌሎችም ምክንያቶች ይኸው አኀዝ እንደሚጨምር ባለሞያው አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ኢትዮጵያዉያንን እየፈተነ ያለው የኑሮ ውድነት
            <description>በምግብ ፍጆታዎች ላይ ቀን በቀን በሚደረጉ የዋጋ ጭማሬዎች ምክንያት መማረራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። የዋጋ ንረቱ እየጨነረ በሚሄድበት ጊዜ የነዋሪዎች ገቢ አለመጨመሩ ችግሩን የበለጠ እንዳወሳሰበው የተናገሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሰውአለ አባተ ናቸው። መፍተሄ የሚያመጡ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን ለመተግበርም በመጀመርያ ሰላም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ማብራርያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አለ ያሉትን “የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት” ለመጠገን መንግሥታቸው የነደፈው የሪፎርም ፖሊሲ በኮቪድ 19፣ አለማቀፋዊ ጫናዎችና ውስጣዊ ጦርነቶች ምክንያት እንደታሰበው እንዳልሄደ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።
በሱዳን በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ዜጎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ
            <description>በሱዳን በቀጠለው ቀውስ የተነሳ ቢያንስ በ25 ሚሊዮን ህዝብ ላይ ከባድ ረሐብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ስጋት መደቀኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም ገለፀ። ቀውሱ በቀጣናው በመዛመቱም በየሳምንቱ ብዙ ሺህ ሱዳናዊያን ድንበር አቋርጠው ወደቻድ እና ወደደቡብ ሱዳን እየተሰደዱ መሆኑን አመልክቷል።
በአሶሽየትድ ፕሬስ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በትግራይ “ከባድ ረኀብ አንዣቧል” ያሉት ጌታቸው ረዳ የዳያስፖራውን ድጋፍ ተማፀኑ
            <description>የትግራይ ክልልን የሰላም ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም አዳጋች የሚያደርግ፣ ከባድ የረኀብ አደጋ እያንዣበበ እንደሆነ ያመለከቱት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ ለትግራይ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ የድጋፍ ጥሪ አቅርበዋል።
“የሰላም ግንባታ እና ፍትሕ በድኅረ ጦርነት ትግራይ” በሚል ርእስ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በድረ ገጽ በተካሔደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ አቶ ጌታቸው ሲናገሩ፣ ሕዝቡን ከረኀብ አደጋ ለመታደግና በጦርነቱ የወደመውን መንግሥታዊ መዋቅር ወደነበረበት ለመመለስ የዳያስፖራ ማኅበረሰቡ ሚና አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሌላው የኮንፈረንሱ ተናጋሪ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ ከባድ የረኀብ አደጋ እንደሚኖር በአቶ ጌታቸው የተገለጸውን ከፍተኛ ስጋት እንደሚጋሩ ጠቅሰው፣ ከብዙ አጋሮቻችንና ለጋሾች ጋራ በትብብር መሥራታችን...</description>
“የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች በድርቁ ምክንያት ወደ ከተሞች እየተሰደዱ ነው”- ዩኤንኦቻ
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ጃናሞራና ጠለምት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከአራት ሺ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ከቀያቸውን ለቀው ወደ ከተሞች መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UN-OCHA) ትናንት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
በሁለቱ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ከ86 ሺ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን እና ከ173 ሺህ በላይ መሰደዳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።
የጃን አሞራ ወረዳ ግብርና ፅ/ ቤት በበኩሉ፣ በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 1ሺ 4 መቶ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ወደ ከተሞች መሰደዳቸውን ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።
ድርቁ ባስከተለው ረኀብ ምክንያት ጠለምት ወረዳን ለቀው አራት ቀን በእግር  ተጉዘው በአጎራባቹ አድርቃይ ከተማ እንደሚገኙ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የተባበሩት...</description>
በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት የረሃብ አደጋን ደቅኗል 
            <description>በሱዳን በመካሄድ ላይ ያለው የሁለት ጀኔራሎች ጦርነት ከካርቱም በስተ ደቡብ ወደምትገኘውና አል-ጃዚራ ወደተሰኘችው ለም አካባቢ ከተዛመተ ወዲህ፣ በአንድ ወቅት ትርፍ ያመርቱ የነበሩ ገበሬዎች ምጽዋት ጠባቂ ሆነዋል።
ገበሬዎቹ ወደ ማሳቸው መሄድ እንዳልቻሉ እና የዘሩትን መንከባከብም ሆነ መሰብሰብ እንዳልቻሉ ለኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።
በሱዳን መደበኛ ሰራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ባለፈው ሚያዚያ ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ፣ አል-ጃዚራ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች መጠለያ እንደሆነበረች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
ጦርነቱ ወደ ደቡብ አቅጣጫ እየተስፋፋ በመምጣቱ ግን፣ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር በአል-ጃዚራ የነበረው ሰላም ደፍርሷል። ዋድ ማዳኒ የተሰኘችውን ከተማ ለመቆጣጠር ውጊያው በመፋፋሙ፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ለመሸሽ...</description>
በረሃብ “138 ሰው ሞቷል” - አፅቢ ወረዳ
            <description>“በረሃብ ምክንያት የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ ነው” ሲል በትግራይ ክልል የአፅቢ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።
"አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ" በሚል የተቋቋመው ኮሚቴ 282 ሚልዮን ብር አሰባስቦ 64 ሺሕ ኵንታል እህል በድርቅ ወደ ተጎዱ አካባቢዎች ማድረስ መጀመሩን ገልጿል።
የአፅቢ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መዝገበ ግርማይ በወረዳው በረሃብ ምክንያት 138 ሰው መሞቱን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።
በወረዳው ደራ የሚባል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃን ክፍለ የዘንድሮን የመሰለ ድርቅ አይተው እንደማያውቁ ጠቁመው አምስት ልጆች ይዘው ለረኃብ መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
“ብዙ አረጋዊያን እናቶች ቤታቸውን ዘግተው ተኝተዋል። ከባድ ረሃብ ስላለ ወጣቱም አካባቢውን ጥሎ እየተሰደደ ነው። ወላጆቻችን፣ እህት ወንድሞቻችን እያየን ከሚሞቱብን በማለት ወደ አረብ...</description>