የፎቶ መድብል - የአሜሪካ ድምፅ
        <description>የፎቶ መድብል</description>
የፎቶ መድብል - የአሜሪካ ድምፅ
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ጉብኝት አደረጉ 
            <description>እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባለፈው ታኅሣሥ ወር መጀመሪያ በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን አሸማጋይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኹለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ ባለበት ወቅት፣ ወደ ሞቃዲሾ ያቀኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድና በሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረፋዱ ላይ ለይፋዊ ጉብኝት ሞቃዲሹ እንደደረሱ፣ የአል ሻባብ እንደኾነ የተገመተ በርካታ ዙር የሞርታር ተኩስ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው አቅጣጫ መከፈቱን በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ቢያንስ አንዱ የሞርታር ተኩስ በአውሮፕላን ማረፊያው ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኝ ጋራዥ ውስጥ ማረፉን ደግሞ ስሙ ያልተጠቀሰ የተቋሙ ባልደረባ ገልጿል። የሞርታር ጥቃቱን...</description>
ባይደን በፓርቲያቸው ጉባኤ ደማቅ አቀባበል ተደረላቸው
የናይል ወንዝ በውድቅዳቂ ቆሻሻ ተሞልቷል
            <description>በአህጉሪቱ ረዥሙ መሆኑ የሚነገርለት እና አሥራ አንድ አገሮችን አቋርጦ የሚፈሰው የናይል ወንዝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥሩ ከ200 ሚሊዮን በላይ ለሚደርስ ሕዝብ ዘላቂ የሕይወት ዋስትና ይሰጣል። ይሁን እንጂ ከወንዙ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች የሚታየው እና እያደርም እየጨመረ የመጣው የሰዎች እንቅስቃሴ የወንዙን ሥነ-ምህዳር ለአደጋ ማጋለጡ ተዘግቧል።
በፓፕዋ ኒው ጊኒ የተራራ ናዳ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎችን ከነሕይወታቸው ቀበረ
            <description>በፓፕዋ ኒው ጊኒ አንድ መንደር ውስጥ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች ከነሕይወታቸው በተራራ ናዳ እንደተቀበሩ፣ አገሪቱ ለተባበሩት መንግሥታት ቢሮ አስታውቃለች፡፡
መንጋሎ የተሰኘው ተራራ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ሲናድ፣ ከሥሩ የሚገኘውን ኢንጋ መንደር ሙሉ ለሙሉ አውድሞ ነዋሪዎቿን ከነሕይወታቸው እንደቀበረ፣ ብሔራዊ የአደጋ መከላከያ ቢሮው በመዲናዋ ፖርት ሞርዝቢ ለሚገኘው የተመድ ቢሮ አስታውቋል።
ናዳው፣ በሕንጻዎች እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት በማድረሱና ዋናው አውራ ጎዳና ሙሉ ለሙሉ በመዘጋቱ፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።
ናዳው አሁንም ቀስ በቀስ መንከባለሉን በመቀጠሉ፣ በአደጋ ሠራተኞች እና ከአደጋው መውጣት በሚችሉት ላይ ስጋትን መደቀኑ ተመልክቷል።
የፀሐይ ግርዶሽ 
            <description>ሜክሲኮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ የፀሐይ ግርዶሽ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 30፣ 2016 ዓ/ም ተከስቷል።
በታይዋን ርዕደ መሬት 7 ሰዎች ሞቱ ከ700 በላይ ቆሰሉ
            <description>ታይዋን ምስራቃዊ  ግዛት ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ከባድ ርዕደ መሬት ደርሶ  ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ከ700 በላይ ቆስለዋል፡፡ በርዕደት መለኪያው ሪክተር ስኬል 7 ነጥብ 2 ባስመዘገበው የመሬት መናወጥ   ከባድ የኤሌክትሪክ  ኃይል መቋረጥም የደረሰ ሲሆን በርካታ ህንጻዎችም ወድቀዋል፡፡ ከታይዋን ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ዘልቆ ተሰምቷል የተባለው ርዕደ መሬት በሀገሪቱ በ25 ዓመታት ከደረሱት ሁሉ ከባዱ ርዕደ መሬት ነው፡፡ በርዕደ መሬቱ በማዕከላዊ ታይዋን አንድ ሕንፃ ሙሉ በሙሉ ሲወድም 15 ህንጻዎች በከፊል ወድመዋል፡፡ ሌሎች 67 የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተለይ ሁዋልያን በተባለቸው የምስራቅ ታይዋን  ከተማ ብቻ  ቢያንስ 26 ህንጻዎች  ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ሲወድቁ  ያዘመሙ ህንጻዎችም አሉ፡፡ በማሕበራዊ መገናኛዎች የወጡ ምስሎች  ሊወድቅ...</description>
የጥምቀት ከተራ በዓል በአዲስ አበባ
            <description>የጥምቀት ከተራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሯል፡፡
የእስራኤል ጦር በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ የቀሩትን የሀማስ ተዋጊዎች ጠራርጎ ለማስወጣት እየሠራ እንደኾነ አስታወቀ 
78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ድባብ 
ከ190 በላይ ሀገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ዓመታዊ ጉባዔ የምታስተናግደው ኒው ዮርክ ከተማ ከጥብቅ የጸጥታ ሥምሪት ጋር መሪዎቹን እያስተናገደች ትገኛለች።
በሞሮኮ የደረሰው የመሬት መንቀጥቅጥ አደጋ 
የማንዴላ ዋሺንግተን የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች የትስስር መርሐ-ግብር
በዋሺንግተን ዲሲ በመከናወን ላይ ይገኛል። ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ማህበረሰብ አጋዥ ፈጠራዎች እና የላቁ ሀሳቦችን ይዘው ብቅ ያሉ ከ700 በላይ ወጣት መሪዎች በዘንድሮው መርሐ-ግብር ተሳታፊ ናቸው።
መርሀ-ግብሩ በአውሮፓዊያኑ 2014 የተጀመረ ሲሆን ፣ ከብዙ ሺ አመልካቾች መካከል የተመረጡ ወጣቶች በዩናይትድ ስቴትስ ለስድስት ሳምንታት የቀለም ትምህርት እና አመራር ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ከማስቻሉ በተጨማሪ የርስ በርስ ትስስር አፍታዎችን ያመቻቻል።
ከስር የተያያዙት ምስሎች የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ስኬታማ ወጣት አፍሪካዊ አሜሪካዊያን ከተሳተፉበት የመክፈቻው ቀን ሥነ-ሥርዓት ላይ የተወሰዱ ናቸው።
ለአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ የአህጉሪቱ መሪዎች ፒተርስበርግ መግባት ጀመሩ
            <description>የአፍሪካ መሪዎች፣ ከሁለተኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ እና የኢኮኖሚ ፎረም አስቀድመው፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ መግባት እንደ ጀመሩ ተነገረ፡፡
የምግብ ደኅንነት እና የቫግነር ወታደራዊ ቡድን የወደፊት ዕጣ፣ የጉባኤው ከፍተኛ አጀንዳ ይኾናል፤ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡
የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት፣ በዓለም አቀፉ መድረክ ተሰሚነቱ እየጨመረ ለመጣውና 1ነጥብ3 ቢሊዮን ለሚደርሰው፣ የአፍሪካ አህጉር ሕዝብ ወዳጅነት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ይኖርበታል፤ ተብሏል፡፡
ለሩሲያ ጥሩ አቀባባል ከሚያሳየው የዓለም ክፍልም፣ አገሪቱ ተጨማሪ አጋሮችን እንደምትሻ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ መሪዎች ልኡካን ቡድን፣ በሩሲያ - ዩክሬኑ ጦርነት ሰላም እንዲመጣ፣ ባለፈው የተጓዙበትን የማደራደር ውጥን፣ በድጋሚ ሊሞክሩት ይችላሉ፤ የሚል ግምት መኖሩም ተመልክቷል፡፡
በሕንድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ጠፋ፤ ፍለጋው ቀጥሏል
            <description>በሕንድ፣ በሳምንቱ ውስጥ ከባድ ዝናም መጣሉን ተከትሎ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ 16 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ፣ የአደጋ ሠራተኞች፣ አሁንም ከነሕይወታቸው በናዳ የተቀበሩ ሰዎችንና አስከሬኖችን ለማውጣት በፍለጋ ላይ ናቸው።
ናዳው፣ ራይጋድ በተሰኘው አውራጃ ከደረሰ በኋላ፣ 75 ሰዎችን በሕይወት ማውጣት እንደተቻለ፣ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሌሎች በሕይወት ያሉ ሰዎች እና አስከሬኖች፣ አሁንም በፍርስራሹ ውስጥ ሳይኖሩ አይቀሩም፤ በሚል ፍለጋው ቀጥሏል።
በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናም ምክንያት፣ ሌላ አደጋ እንዳይከሠት በመስጋት፣ ፍለጋው ተቋርጦ ነበር። በአደጋው አካባቢ ከሚገኙ 50 ቤቶች ውስጥ 17 የሚኾኑት፣ በመሬት መንሸራተቱ ተቀብረዋል፤ ሲሉ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በሕንድ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ፣ ከ100 በላይ ሰዎች፣ ከባድ ዝናም...</description>
የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የስፖርት ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል) በዳላስ
            <description>በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን 40ኛ ዓመቱን በዳላስ ቴክሳስ - ዋይሊ ስታዲዬም እያከበረ ይገኛል። ይኸው ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል)፣ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓመታዊ መገናኛ ሆኖ አራት ዐሥርት ዓመታትን ዘልቋል፡፡
ዘንድሮም፣ በባህል፣ በመዝናኛ፣ በንግድ፣ በበጎ አድራጎት፣ በፖለቲካ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ውስጥ ተሳታፊ የኾኑ አካላት፣ ከመላ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጡ በሺሕዎች ከሚገመቱ በትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋራ መስተጋብር ይፈጥሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ግሪክ በጀልባ መገልበጥ ላለቁት ስደተኞች የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ዐወጀች
            <description>ስደተኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ጀልባ፣ ትላንት ረቡዕ፣ በግሪክ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጦ፣ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ፣ ግሪክ፥ የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ዐውጃለች።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ በግሪክ ከደረሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ እንደኾነ በተገለጸው በዚኽ የጀልባ መገልበጥ አደጋ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ቢረጋገጥም፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግን፣ እስከ አሁን ያሉበት ባለመታወቁ፣ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል፣ የግሪክ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በጀልባው ተሳፍረው ከነበሩት አብዛኞቹ፥ ከግብፅ፣ ሶሪያ እና ፓኪስታን የመጡ እንደኾኑ ተነግሯል።የግሪክ ፕሬዚዳንት ካትሪና ሳኬላሮፑሉ፣ ከአደጋው ተርፈው፣ ካላማታ በተሰኘች የግሪክ ከተማ ወደሚገኝ መጠለያ የተወሰዱትን ስደተኞች ሲጎበኙ፣ የከተማዋ ከንቲባ ታናሲስ ቫሲሎፖለስ፣ ስደተኞቹን ለመርዳት የተለያዩ...</description>
የሰደድ እሳት ጢስ በካናዳ እና በዩናይትድ ስቴትስ የጤና ስጋት ደቅኗል 
            <description>ከካናዳው ሰደድ እሳት የሚወጣው ጢስ፣ የምሥራቃዊ እና የማዕከላዊ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶችን እያዳረሰ ነው፡፡ በምሥራቃዊው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ጠርዝ ላይ ያሉት የክፍላተ ግዛቷ ትምህርት ቤቶች በሙሉ፣ የደጅ ላይ እንቅስቃሴዎችን ሰርዘዋል፡፡ ነዋሪዎች፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ከመዘዋወር እንዲቆጠቡም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡  
የምሥራቅ ካናዳው ሰደድ እሳት፣ ወትሮ ከሚነሣበት የበጋው ጊዜ፣ ቀደም እና ጠንከር ብሎ ተከሥቷል፡፡ ደረቁ እና ሞቃቱ የአየር ኹኔታ፣ ገና ለወራት እንደሚቀጥል ሲተነበይ፣ ይህ ዓመት ለካናዳ፥ ከቀደምቱ የበዛ ሰደድ እሳት የሚመዘገብበት እንደሚኾን ስጋት አሳድሯል፡፡ 
ሰደድ እሳቱ፣ ዐሥሩንም የካናዳ ክፍላተ ሀገር እና ግዛቶች ያዳረሰ ሲኾን፣ ከሁሉም የበዛው ያገኛት ግን፣ መብረቅ በየቦታው እሳት የለኮሰባት ኩቤክ ክፍለ ሀገር እንደኾነች...</description>
የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በድጋሚ ምርጫ አሸነፉ
አንድ የዕቃ መጫኛ መኪና ከዋይት ሃውስ አጥር ጋር ተጋጨ
            <description>አንድ የቤት ዕቃ መጫኛ መኪና ትናንት ማምሻውን በዋይት ሃውስ አጠገብ ያለን የደህንነት አጥር ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ተጋጭቶ መያዙን የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ኃይል፣ ሲክረት ሰርቪስ አስታውቋል።
የመኪናው የኋላ ዕቃ መጫኛ በር በሮቦት ተከፍቶ፣ በውስጡ ፈንጂም ሆነ ሌላ አድገኛ ነገር እንደሌለው ፖሊስ አረጋግጧል። የናዚ ስዋስቲካ ባንዲራ ከመኪናው ውስጥ እንደተገኘ ተዘግቧል።
የሚዙሪ ግዛት ነዋሪ የሆነው የ 19 ዓመቱ ወጣት፣ ሳይ ቫርሺት ካንዱላ መኪናውን ሆን ብሉ ከደህንነት አጥሩ ጋር ሳያጋጭ እንዳልቀረ የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ኃይል ገልጿል። ክስ ይመሠረትበታልም ተብሏል።
ከዋይት ሃውስ አቅራቢያ የሚገኘው የሄይ አዳምስ ሆቴል እንግዶች ለደህንነታቸው ሲባል እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።
ግለሰቡ፣ ፕሬዚዳንቱ እና ምክትል ፕሬዝደንቱ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ላይ አደጋ ለማድረስ ወይም...</description>
ትንሣኤ በኢትዮጵያ
የፈረንሳዩ ማክሮን ቻይና ይገኛሉ
            <description>ቻይና በዩክሬንና በሌሎችም ግጭት ባሉባቸው የዓለም ክፍሎች ሰላምን በተመለከተ በጋራ ሃላፊነት እንድትወስድ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን በሚያገኙበት ወቅት አጽንኦት እንደሚሰጡት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ተናግረዋል፡፡
በቻይና የፈርንሳይ ኤምባሲ በመገኘት ለአገራቸው ዜጎች ንግግር ያደረጉት ማክሮን፣ ዩክሬን፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን፣ በተለይም ሰላምን በሚመለከት ቻይና በጋራ ሃላፊነት የምትወስድበትን ሁኔታ ከፕሬዚዳንት ሺ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ትኩረት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል፡፡
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን ከማክሮን ጋር አብረው ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓን አንድነት ለማሳየት ነው ተብሏል፡፡
በጉብኝታቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደው ጦርነት ዋና አጀንዳ እንደሚሆን...</description>