ሃኪምዎን ይጠይቁ - የአሜሪካ ድምፅ
ሃኪምዎን ይጠይቁ - የአሜሪካ ድምፅ
የፓርኪንሰን’ስ በሽታ ምንነት እና ሕክምና
ፓርኪንሰን’ስ ውስብስብ እና አልፎ አልፎም በቅጡ መረዳት የሚያዳግት እና በአንጻሩ በዓለም ዙሪያ አያሌ ሚሊዮኖች ለፈተና የሚዳርግ የሕመም ዓይነት ነው።
“ቀስ በቀስ ሥር እየሰደደ እና እየተባባሰ የሚሄድ፣ በተለይም የአካል እንቅስቃሴን የሚቆጣጠረውን የአንጎል ክፍል የሚያጠቃ እና ከነርቭ ስርዐት መታወክ ጋራ የተዛመደ የጤና ሁከት ነው” የሚሉን ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የነርቭ እና የአእምሮ ሃኪም ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ናቸው። ፕሮፌሰር ዮናስ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትሱ ‘ባሮ የነርቭ ሕክምና’ ተቋም መምህር እና ተመራማሪም ናቸው።
የባለሞያውን አስተያያት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የዓይን ማዝን ለማጥፋት የተሄደው ረዥም ጉዞ ... የዓይን ሃኪሙ ማስታወሻ
ለረዥም ዓመታት በዓይን ሃኪምነት ያገለገሉ ናቸው። ከዚህም ውስጥ የሚበዛው በሕክምና ካልተረዳ ለአይነ ስውርነት እስከመዳረግ የሚደርሰውን የአይን ማዝ በሽታ ለመዋጋት ለዓመታት በተካሄደው ዘመቻ ያደረጉት ነው። ዶ/ር ወንዱ ዓለማየሁ።
ሊድን ስለሚችለው የዓይን በሽታ፣ የዐይን ብርሃንን ማዳን የመሰለ ድንቅ ሥራ የሚሰጠውን የመንፈስ እርካታ እና ጉዞው የሚጠይቀውን ቀሪ ሥራ ጨምሮ ሙሉውን ከተከታዩ ወግ ይከታተሉ።
ከጆሮ ውስጥ የሚሰማ አዋኪ ድምጽ ምንነት እና ሕክምናው
            <description>“ጆሮዬ ላይ ጭው የሚል ኃይለኛ እና አዋኪ ድምጽ፣ ለየት ያለ ድምጽ ይሰማኛል” ሲሉ ሰዎች በተለያየ መልክ የሚገልጹት ችግር ነው።
ይሁን እንጂ የተለያዩ ሰዎች የሚሰማቸው ድምጽ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል ባለሞያ ዎች ያስረዳሉ።
“በእንግሊዝኛ በሕክምናው አጠራር ‘tinnitus’ በመባል የሚታወቀው ይህ ሁኔታ የሚከስታቸው ድምጾች እጅግ ብርቱ ወይም ቀላል ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት ለሞያዊ ማብራሪያ የጋበዝናቸው የአንገት በላይ ልዩ ሃኪም እና የሕክምና መምሕሩ ዶ/ር በላቸው ተሰማ ናቸው።
“የሚያቃጭል፣ ወይም ‘ጥዝዝ’ የሚል፣ እንደ ነፋስ ያለ አለያም ሌላ ለየት ያለ ድምጽ ሊሰማም ይችላል’ ይላሉ። ቁጥሩ ከ15 እስከ 20 በመቶ የሚሆን ሰው የሚያጠቃ እና በጣም የተለመደ ነው። 
 የማለሞያውን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 
"እጅግ ከፍተኛ" የሰውነት ክብደትን ለማከም የዋሉት ዐዲሶቹ መድኃኒቶች የሚሹት ጥንቃቄ
            <description>እንደ ብርቱ የጤና ችግር የሚታየው "እጅግ ከፍተኛ" የሰውነት ክብደት፣ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ልዩ ልዩ የጤና ጠንቆች እንዳሉ ይታመናል።
በሕክምናው ዓለም የእንግሊዘኛው አጠራር ‘ኦቤሲቲ’ በመባል የሚታወቀውን ይህን ‘እጅግ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት’ በማከሙ ረገድ፣ "ከአሁን ቀደም ያልታየ" የተባለን ውጤት ያሳዩትና ከፍተኛ ትኩረት የሳቡት እነኚኽ መድኃኒቶች፥ “የጥቅማቸውን ያህል በሐኪም የቅርብ ክትትል እና በጥንቃቄ መወሰድ ያለባቸው ናቸው” - እንደ ባለሞያዎች ማብራሪያ።
የምሽቱ "ሐኪምዎን ይጠይቁ" ዝግጅት፣ ይኸው የጤና ችግር በሕክምና የሚረዳባቸውን መድኃኒቶች ምንነት፣ ፋይዳ እና ፈተናዎች የሚፈትሽ የባለሞያ ትንታኔን ይዟል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለሞያው ዶክተር አቤል ተካ ናቸው።
‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?
            <description>በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል ይሆን? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተደረሰባቸው ያሉ ከበሽታው ጋር የተዛመዱ ሁኔታዎች ካሁን ቀደም ስለሕመሙ ይታመኑ የነበሩ እውነታዎችን ጭምር በእጅጉ እየቀየሩ መሆናቸው ይነገራል።
"ለመሆኑ ከስኳር በሽታ ሙሉ በሙሉ ሊዳን ይችላል?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “አዎንም፣ አይደለምም፤ ነው” የሚሉን ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለ ሞያው ዶ/ር አቤል ተካ ናቸው።
”‘ኢንሱሊን’ የተባለውን ሰውነት የሚያመነጨውን ንጥረ ነገር የሰውነት አካላት በአግባቡ መጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር በወጉ መረዳት፤ የተለያዩ ውስብስብ ችግሮች የሚያስከትለውን የስኳር በሽታ ምንነት...</description>
የእግር ጉዞ ማዘውተር ለአንጎል ጤና የሚያስገኘው የላቀ ጠቀሜታ
የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራ አለያም ሌሎች መሰል ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ ማድረግ ለአንጎል ጤና ከፍ ያለ ጥቅም የሚያገኝ መሆኑን በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ የሳይንሳዊ ምርምር ጽሑፍ አመለከተ። የአንጎልን አሠራር ማቀላጠፍ እና የዓመታት ወጣትነት ማጎናጸፍ መቻሉ ተገልጿል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ የነርቭና የአእምሮ ሃኪም፣ እንዲሁም በባሮ የነርቭ ሕክምና ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። ፕሮፌሰር ዮናስ ካሁን ቀደም ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎች ዕድሜያቸው ከሰባ ዓመት በላይ የሆኑ አረጋውያን በተመሳሳይ ቀላል የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ ከመጃጀት ጋራ ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችን በመከላከል የሚረዱ መሆናቸውን ያረጋገጠ ለከፍተኛ እውቅና የበቃ ሳይንሳዊ የምርምር ሥራ አካሂደዋል።
ሞያዊ ትንታኔውን ከተያያዘው...</description>
ቀለማት አጥርቶ የመለየት ፈተና
የምናየው የቀለም አይነት በግልጽ እስከታየን ድረስ በእርግጠኝነት መናገር ብዙም አያዳግትም። ይሁንና ቁጥሩ በግምት ስምንት በመቶ ለሚደርሰው ሕዝብ ግን እውነታው የተለየ ነው። ቀለማት ተቀላልቅለው በሚታዩበት ምስል ውስጥ አጥርተን የማናየው የቀለም ዓይነት፣ ምስሉ ከምናየው የተለየ ሊኾን ይችላል።
በዚያ ላይ ችግሩ እንዳለ የምናውቅበት አጋጣሚ እስኪፈጠር ድረስ፣ ችግሩን ላናውቅ የምንችልበት አጋጣሚ አለ። በተለይ በወንዶች ላይ የሚከሰተውን ይህን ሁኔታ ምንነት እንዲያስረዱን ለዛሬ ሀኪሞን ይጠይቁ ፕሮግራም ዶ/ር ትልቅ ሰው ተሾመ ጋብዘናል።
በሕክምና የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ
ዋና መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው “ፒፕል ቱ ፒፕል” ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የአርሊንግተን ዋና ከተማ የተመሰረተበትን ሃያ አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ዓመታዊ የሕክምና ሳይንስ ጉባኤው አካሂዷል። አብዛኞቹ አባላቱ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሞያዎች ቢሆኑም፤ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የሕክምና ባለ ሞያዎችም ለዓመታት ተሳትፈውበታል።
ከሕክምና አገልግሎቶች እና የህክምና ትምሕርት ተሳትፎዎቹ በተጨማሪም በሌሎች ርዳታ የሚሹ ማኅበራዊ ጉዳዮች አስተዋጽኦ ሲያደርግ የቆየ ድርጅት ነው። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ከድርጅቱ አመራር አባላት ጋራ ውይይት አካሂደናል።
ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
አዲስ መድሃኒት - ለድህረ ወሊድ የድብታ ሕመም ሕክምና 
አንዳንድ እናቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ለመንፈስ ጭንቀት የሚጋለጡበት ሁኔታ ይከሰታል።
ለድህረ ወሊድ የድብታ ሕመም የተጋለጡ እናቶች ከፍተኛ የስሜት መዋዠቅ፣ ጥልቅ ሃዘን፣ የበረታ ድካም፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ጭንቀት እና ልጃቸውን በወጉ የመንከባከብ ችግር ጭምር ሊገጥማቸው ይችላል።
ሳምንታዊው ‘ሃኪምዎን ይጠይቁ’ ይህን ድሕረ ወሊድ የሚከሰት ሕመም ለማከም የሚረዳ አዲስ መድሃኒት ምንነት ይመለከታል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን በዩናይትድ ስቴትሱ የምግብ እና የመድሃኒቶች ቁጥጥር ባለ ሥልጣን በምርምር ባለሞያነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ዶ/ር አሌክስ አካሉ ናቸው።
ዶ/ር አሌክስ’ን ያነጋገገረው የፕሮግራሙ አዘጋጅ እና አቅራቢ አሉላ ከበደ ነው።
'መተንፈስ' ለጤና!
ቀላል እና ያለ አንዳች ሃሳብ ቀኑን በሙሉ ሳናቋርጥ የምናደርገው ድርጊት መሆኑ፣ ኃያል የሕይወት ምስጢርነቱን ለመዘንጋት ያቃርበናል። በተፈጥሮ ልማድ ከማድረግ ያለፈም አስክናጣው ድረስ የሚገባውን ዋጋ የሚመጥን ቦታ አንሰጠውም።
በአንዲት ቀን ውሎ ብቻ በአማካይ ፳ ሺሕ ለሚጠጋ ጊዜ ያለ አንዳች የተለየ ጥረት ማድረጋችን፤ አየር ስበን ወደ ሳምባችን እናስገባ እና ከሳምባችን ያለውን የቀደመውን ትንፋሽ እንለቀዋለን። እናም ሌላ ትኩስ አየር መማግ ... የማይቋረጠው ዑደት ይቀጥላል።
"በደመ ነፍስ" ሊባል በሚችል ዘይቤ የምንፈጽመውን ድርጊት፣ ሆን ተብሎ እና በአግባቡ ወደ ሚደከናወን የአተነፋፈስ ዘዴ ስንወስደው ግን፤ 'መተንፈስ' ለጤና ተጀመረ ማለት ነው። ካሁን ቀደም ይበልጡን የምሥራቁ ዓለም ፍልስፍና አይነተኛ ዘዬ የነበረው ጥበብ ወደ ዘመናዊው ሳይንስ ዓለም ከዘለቀም...</description>
‘የዝንጀሮ ፈንጣጣ’ ... ‘ኤምፖክስ’ ምንድነው? 
            <description>ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እንዳይቀሰቀስ በሚል በብዙዎች ዘንድ ሥጋት ያሳደረው ‘ኤምፖክስ’ በሁለት ዓመታት ዕድሜ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለምን ትኩረት ስቧል። አሳሳቢነት የደቀነው እና በስፋት እያነጋገረ ያለው፡ በልማድ አነጋገር ‘የዝንጀሮ ፈንጣጣ’ ... በእንግሊዝኛው አጠራር ‘ኤምፖክስ’ በመባል የሚታወቀው ይህ በሽታ በራሱ ምንድነው?
ሃኪምዎን ይጠይቁ በተከታታይ ቅንብሩ፣ የቫይረሱን መተላለፊያ መንገዶች፣ የበሽታውን ምልክቶች እና ራሳቸውን የለወጡ አዳዲስ ዝርያዎች፤ እንዲሁም ክትባት እና ህክምና ይመለከታል።
ዶ/ር ነጋ አሊ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የሜሪላንድ ክፍለ ግዛቷ የራክቪል ከተማ የሼዲ ግሮቭ የአድቬንቲስት የጤና እንክብካቤ ክሊኒክ የተላላፊ በሽታዎች እና የጽኑ ሕሙማን ሃኪም ናቸው።
ክፍል አንድ:- ‘ኤምፖክስ’ ምንድን...</description>
‘የዝንጀሮ ፈንጣጣ’ ... ‘ኤምፖክስ’ ምንድነው? 
            <category>ሃኪምዎን ይጠይቁ</category><enclosure url="https://gdb.voanews.com/6166f502-eb82-45fb-88d3-76519538b540_w800_h450.jpeg" length="0" type="image/jpeg"/>
ጭንቀትን ለማርገብ... 
            <description>ጭንቀት የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም በማዳከም ለተለያዩ የህመም ዐይነቶች ማጋለጡን አስመልክቶ የሳይንሱን ዓለም እይታ የቃኘው የምሽቱ ሃኪምዎን ይጠይቁ በተከታታይ ቅንብሩ ጭንቀትን ለማርገብ የሚያግዙ ብልሃቶች ጨምሮ ከባለ ሞያ ጋር የተካሄደ ምልልስ ይዟል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የዩናይትድ ስቴትሱ ባሮ የነርቭ ሕክምና ተቋም መምህር፣ ተመራማሪና የነርቭ እና የአእምሮ ሃኪሙ ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ናቸው።
 ክፍል አንድ:- ጭንቀት እና ጣጣው 
 ክፍል ሁለት:- መላው ምንድ ነው?
የኮሌራ ወረርሽኝ በበርካታ ሃገራት መስፋፋቱ ተነገረ
            <description>ከጥር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስካለፈው ሐምሌ ወር ድረስ ባሉት ጊዜያት በ26 ሃገራት የሚገኙ ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
በወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁት ውስጥ ድርጅቱ ምሥራቃዊ የሜዲትሬኒያን ክልል ብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ የታየ ሲሆን ቀጥሎ ወረርሽኙ በብዛት የተስተዋለበት ደግሞ የአፍሪካ ክልል ነው።
በአፍ የሚሰጠው የኮሌራ ክትባት በከፍተኛ ደረጃ እጥረት መከሰቱ፣ ለወረርሽኙ የሚሰጠውን ምላሽ ደካማ እንዳደረገ የጤና ድርጅቱ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት 18 ሃገራት 105 ሚሊዮን ክትባቶች እንደሚያስፈልጓቸው ጥያቄ ማቅረባቸውም ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት አንደኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን እንዳባባሰ የጤና ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ኮሌራ የ316...</description>
ባይደን ለካንሰር ምርምር ተጨማሪ 150 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቁ
            <description>ካንሰር ዕጢዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስወገድ የሚረዳ ቴክኖሎጂን ለማበልጸግ ይውል ዘንድ ተጨማሪ 150 ሚሊዪን ዶላር የፌዴራል መዋዕለ ነዋይ መመደቡን ፕሬዝደንት ባይደን ትላንት አስታውቀዋል።
ገንዘቡ በአሜሪካ ላሉ የካንሰር ምርምር ተቋማት የሚውል ሲሆን፣ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች የካንሰር ዕጢን በተሻለ መንገድ ማስወገድ እንዲችሉ የሚረዳ ቴክኖሎጂን ለማበልጸግ የሚውል እንደሆነ ፕሬዝደንቱ አመልክተዋል።
በኒው ኦርሊየንስ ቱሌን ዩኒቨርስቲ የሚገኘውን የካንሰር ምርምር ክፍልን የጎበኙት ባይደን፣ አበረታች ውጤት ማየታቸውንና ሐኪሞች ሌሎች የውስጥ ሰውነት ክፍሎችን፣ ነርቮችና የደም ሥርን ሳይጎዱ የካንሰር ዕጢውን ማሰወገድ የሚችሉበትን ሁኔታ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በፕሬዝደንት ባይደንና በቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን የሚመራውና “ካንሰር ሙንሻት” በሚል የሚጠራው...</description>
ፈንጣጣ በአህጉሪቱ አደገኛ የጤና ስጋት መደቀኑን የአፍሪካ ኅብረት አስጠነቀቀ
            <description>በተለምዶ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሚባል የሚታወቀው የፈንጣጣ ዐይነት ወረርሽኝ በአፍሪካ አህጉር እየተስፋፋ መምጣቱን እና ከፍተኛ የጤና ስጋት መደቀኑን በአፍሪካ ኅብረት ሥር የሚተዳደረው ‘የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከላት’ አስታውቋል።
ወረርሽኙ፤ ተውሳኩ መጀመሪያ በእ.አ.አ 1970 የተከሰተባትን የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጨምሮ በበርካታ ሃገራት እየተዛመተ እንደሚገኝ ተቋሙ ገልጿል።
“የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአህጉሪቱ አጣዳፊ የሕዝብ ጤና ስጋት ነው” ሲሉ የተቋሙ ኃላፊ ዣን ካሲያ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።
ተውሳኩ ድንበሮችን በመሻገር በመላ አህጉሪቱ በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዳወከና ቤተሰቦችን እንደበተነ ሃላፊው ጨምረው አስታውቀዋል።
ተቋሙ እንደሚለው፣ እስካለፈው ሳምንት በተገኘው መረጃ መሠረት 38ሺሕ 465 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ ከእ.አ.አ 2022...</description>
የቤት ውስጥ ሕክምና ፋይዳ እና ከወዲሁ መታሰብ ያለባቸው አበይት ጉዳዮች
ዘመን የጠገቡት የባሕል መድሃኒቶች እና የቤት ውስጥ ሕክምና ዘዴዎች አብላጫ ቁጥር ያለው የማኅበረሰብ ክፍል ሲገለገልባቸው የኖሩ የመሆናቸውን ያህል ጠቀሜታቸው እያደር በዘመናዊ ሳይንስ እየተለየ እና ፋይዳቸውም እየጎላ መምጣቱ ይታወቃል። በአንጻሩም “ለመሆኑ የትኞቹ የባሕል መድሃኒቶች እና የቤት ውስጥ ሕክምና ዘዴዎች መድሃኒቶች ለየትኛው የሕመም ዓይነት ሕክምና ይረዳሉ? በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን በምንወስድበት እና በትይዩው የባሕል ሕክምና ስንጠቀም አለያም ከምናዘወትራቸው የምግብ አይነቶች የትኞቹን ስንመገብ በተለይ ማጤን ያሉብን ጉዳዮች ምንድ ናቸው?” የሚሉት ሳምንታዊው ‘ሃኪምዎን ይጠይቁ’ ለምሽቱ ትኩረት ያደረገባቸው ጭብጦች ናቸው።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን በዩናይትድ ስቴትሱ የምግብ እና የመድሃኒቶች ቁጥጥር ባለ ሥልጣን በምርምር ባለሞያነት በማገልገል ላይ...</description>
ወባ ከግጭት በበለጠ ሰውን እየገደለ መኾኑን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ
            <description>በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተከሠተው የወባ ወረርሽኝ፣ “የሰው ሕይወትን እየቀጠፈ ነው፤” ያሉ ነዋሪዎች፣ በተለይም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ክፉኛ መዛመቱንና ለዓመታት የቀጠለው ግጭት ከሚያደርሰው ጉዳት በበለጠ ሰዎችን እየገደለ መኾኑን አመልክተዋል።
የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው በዞኑ የሚገኙ አንድ የሕክምና ዶክተርም፣ ከታካሚዎቻቸው መካከል 90 በመቶዎቹ ከባድ የወባ ምልክት ያለባቸው ታማሚዎች መኾናቸውን ጠቁመዋል።
በተለያዩ ዞኖች ያለው የጸጥታ ችግር እና አለመረጋጋት፣ የወባ ትንኝን በመከላከል እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩንም ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶር. ተስፋዬ ክበበው ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የወባ በሽታ ስርጭት፣ ባለፉት ሳምንታት በዕጥፍ መጨመሩን ገልጸው፣ ችግሩን የሚመጥን ርምጃ መውሰድ...</description>
የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ የሕክምና መጀመሪያ እና መጨረሻ  
            <description>በአመዛኙ የሚገባውን ሥፍራ የተነፈገ ቁልፍ የሕክምና ዘርፍ ነው፡፡ ከልብ እና የሆድ እቃ የሕመም አይነቶች፣ ጭንቀት እና የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የስኳር በሽታ አለያም በደም ውስጥ የስብ መጠን ከፍ ማለት - ሁሉም በአናኗር ዘይቤ ለውጥ ይረዳሉ።
“ብዙዎቹ እነዚህ መድሃኒቶች ተጠንተው ‘በሽታውን ይፈውሳሉ’ ተብለው መጀመሪያውኑ ሲታሰቡ፣ የኑሮ ዘይቤ ለውጦችም በዚያ ሙከራ ወቅት አብረው ተጠንተው ነው ለሕክምናው እንዲውሉ  የሚደረጉት። ይህም ማለት ለአንድ ሰው ዝም ብለን መድሃኒቶች ብቻ በምንሰጥበት ወቅት ከሚያስፈልገው የሕክምና እንክብካቤ ቀንሰን እንደመስጠት የሚቆጠር ነው። ለዚህም ምክኒያቱ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ባለመካተቱ!” ሲሉ የልብ በሽታዎች ልዩ ሃኪሙ ዶ/ር ውብሸት አየነው ያስረዳሉ።
አንዳንድ የሕመም አይነቶችም “ማድረግ ያለብንን ባለማድረግ፣ የሌለብንን ደግሞ...</description>
‘ኒውሮፓቲክ ፔይን’ ምንድነው?
            <description>በሕክምናው አጠራር በእንግሊዝኛ ‘ኒውሮፓቲክ ፔይን’ ይሰኛል። የተለያዩ መንስኤዎች ቢኖሩትም በአመዛኙ በነርቭ ሥርአት ላይ በሚደርስ ጉዳት የሚመጣ እና ብርቱ የሥቃይ ስሜት የሚያስከትል የበሽታ ዓይነት ነው።
“በውስብስብ ተፈጥሮው የተነሳ በምርመራ ጭምር ለማወቅ አዳጋች ሊሆን ይችላል” ይላሉ ከፍተኛ የነርቭ ሃኪሙ ዶ/ር እናውጋው መሃሪ።
እንደ ስኳር በሽታ አለያም ከአንድ ቦታ ተነስቶ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የሚሰራጭ አለያም የሚጠዘጥዝ የሕመም ስሜት እንደሚያስከትል ያስረዱት ዶ/ር እናውጋው፣ አንዳንዴ የሕመም ሥሜቱ ያለበትን የሰውነት ክፍል በእጅ መንካት ብቻ ሥቃዩን ሊያብብስ እንደሚችል ያብራራሉ።
የሕክምናው ዋና አላማም የሥቃይ ስሜትን መቀነስ እና በሕመሙ ሳቢያ በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያከተለውን የተመሳቀለ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን፤ በአጭሩም ሕመሙን ነጥሎ...</description>